ሮማንሽ
From Wikipedia
ሮማንሽ ወይም ሩማንች (Rumantsch) ከስዊስ አገር 4 ብሐራዊ ቋንቋዎች 1ዱ ሆኖ ሌሎቹ 3 ጀርመንኛ ጣልኛና ፈረንሳይኛ ናቸው። ከሮማይስጥ የታደገ ቋንቋ በመሆን የሮማንስ ቋንቋ ቤተሠብ አባል ነውና በተለይ የሚመስለው ፈረንሳይኛ ወይም እጣልኛ ነው። የሚናገረው በግራውብውንደን (ግሪዞን) ካንቶን ስዊስ በሚኖሩ 50,000 እስከ 70,000 ሰዎች ነው። ይህ ከስዊስ አገር ሕዝብ ብዛት 1% ብቻ ሲሆን ከስዊስ አገር ብሐራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሹ ነው። እንኳን በስዊስ አገር ከሚኖሩት ስርቦ-ክሮዌሽኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ብዛት (111,000) በግማሽ ያንሳል።
በስሜን እጣልያ አገር ዛሬ ለሚናገሩ ቋንቋዎች ለፍሪዩልያንና ለላዲን ቅርብ ዘመድ ነው።
ምሳሌዎች፦
- Jau hai num x (ያው አይ ኑም x) - ስሜ x ነው (ስም x አለኝ)።
- Jau sun ad uras (ያው ሱን አድ ኡራስ)- በጊዜ ላይ ነኝ።
- giuven (ጁቨን) - ወንድ ልጅ፣ giuvens (ጁቨንስ) - ወንድ ልጆች
- il giuven (ኢል ጁቨን) - ወንድ ልጁ፣ ils giuvens (ኢልስ ጁቨንስ) - ወንድ ልጆቹ
- giuvna (ጁቭና) ሴት ልጅ፣ giuvnas (ጁቭናስ) ሴት ልጆች
- la giuvna (ላ ጁቭና) ሴት ልጂቱ፣ las giuvnas (ላስ ጁቭናስ) ሴት ልጆቹ
- ያልተለመደ ብዙ ቁጥር፦ um (ኡም) - ሰው፣ umens (ኡመንስ) - ሰዎች