ሴኔጋል
ከWikipedia
|
|||||
ዋና ከተማ | ዳካር |
||||
ብሔራዊ ቋንቋ(ዎች) | ፈረንሳይኛ | ||||
መሪዎች ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
አብዱላዬ ዋዴ ሼክ ሃጂቡ ሱማሬ |
||||
የነጻነት ቀን | ሰኔ 13 ቀን 1952 (June 20, 1960 እ.ኤ.አ.) |
||||
የመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.) |
196,190 (ከዓለም 85ኛ) | ||||
የሕዝብ ብዛት (በ2002) |
10,284,929 (ከዓለም 75ኛ) | ||||
የገንዘብ ስም | CFA ፍራንክ | ||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | ||||
የስልክ መግቢያ | +221 |
ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል።
[ለማስተካከል] ታሪክ
በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ።
ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ።
በፌብሩዋሪ 1, 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች።
አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል።
በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች |
ሊቢያ| ላይቤሪያ| ሌሶቶ| የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ| ማሊ| ማላዊ| ማዳጋስካር| ሞሪሸስ| ሞሪታኒያ| ሞሮኮ| ምዕራባዊ ሣህራ| ሞዛምቢክ| ሩዋንዳ| ሱዳን| ሲሸልስ| ሳን ቶሜና ፕሪንሲፔ| ሴየራ ሌዎን| ሴኔጋል| ስዋዚላንድ| ሶማሊላንድ| ሶማሊያ| ቡሩንዲ| ቡርኪና ፋሶ| ቤኒን| ቦትስዋና| ቱኒዚያ| ታንዛኒያ| ቶጎ| ቻድ| ኒጄር| ናሚቢያ| ናይጄሪያ| አልጄሪያ| አንጎላ| ኢትዮጵያ| ኢኳቶሪያል ጊኔ| ኤርትራ| ኬንያ| ኬፕ ቨርድ| ካሜሩን| ኮሞሮስ| ኮት ዲቯ| ኮንጎ ሪፑብሊክ| ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ| ዚምባብዌ| ዛምቢያ| ዩጋንዳ| ደቡብ አፍሪካ| ጅቡቲ| ጊኔ| ጊኔ-ቢሳው| ጋምቢያ| ጋቦን| ጋና| ግብፅ| |