ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ
From Wikipedia
ግርማዊ፡ ቀዳማዊ፡ ዐፄ፡ ኃይለ፡ ሥላሴ፡ ንጉሠ፡ ነገሥት፡ ዘኢትዮጵያ፣ የተፈሪ መኰንን ስመ-መንግሥት ነበር። ሞዓ፡ አንበሣ፡ ዘእምነገደ፡ ይሁዳ፡ ሥዩመ፡ እግዚአብሔር፣ የሚለው የሰሎሞናዊው ሥረወ-መንግሥት ነገሥታት መጠሪያም በንጉሠ-ነገሥቱ አርማ እና ሌሎች ኦፊሴላዊ ጽሑፎች ላይ ከመደበኛው ማዕረግ ጋር ይጠቀስ ነበር።
ተፈሪ መኰንን ሐምሌ 16 ቀን 1884 ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ1899 የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ1903 ዓ.ም. የሀረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ።
[ለማስተካከል] ጥቅስ
- << አንዳንድ ሰዎች የሕይወቴን ታሪክ ጽፈው ባለማወቅ ወይም በመሳሳት ወይም በመቀኝነት ዕውነትን አስመስለው ለሌሎች እንዲመስል ቢሞክሩም የዕውነተኛውን ነገር ከሥፍራው ሊያናውጡት አይችሉም። >>
- -- ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ (መቅደም)