ሌቱም አይነጋልኝ
ከWikipedia
በውቤ በረሃ ተጀምሮ በ ፰፱፻፶፯ (1957) ፈረንሳይ ሃገር የተጻፈው ሌቱም አይነጋልኝ ደራሲው ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር መጽሃፉ እንዲታተም
(እሱ ደንታ ባይኖረውም...በመጽሃፉ ውስጥ እንደጠቀሰው "እኔኮ ያደረብኝ ለዘብተኛ ልዝብ ዛር በበቂ ደሞዝና ትርፍ ስኣት እያንበሻበሸ ስላበረታታኝ ጻፍኩ'ንጂ ይታተም አይታተም ደንታ አልነበረኝም።")
ወዳጆቹ ቢሞክሩም በመንግስት ሳንሱር "ለአንባቢያን የማይገቡ ግልጽ የወሲብ ቃላቶች አሉበት" በሚል ምክንያት እየታገደ ለሃያ አምስት አመታት በአንባቢዎቹ እጆች በእጅ እየተገለበጠ ሲነበብ ኖሩዋል።
በአሁኑ ሰኣት በመጀመሪያ እነዛ ወሲባዊ ቃላቶችን "ለስለስ" ባሉ ቃላቶች በመተካት ለአንባቢያን እንዲደርስ መጽሃፉ ታትሞ ለገብያ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በሃገራችን አቆጣጠር በ1999 ያንኑ መጽሃፍ ደራሲው የተጠቀመባቸውን ቃላቶች ትክክለኛ ግልባጭ የያዘ " ሌቱም አይነጋልኝ...እንደ ወረደ " መጽሃፍ ለአንባቢያን ቀርቧል።