መስከረም 2
ከWikipedia
መስከረም 2 ቀን: ብሄራዊ ቀን በኬፕ ቨርድ...
[ለማስተካከል] ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- 1184 - በመስቀል ጦርነት የእንግሊዝ ንጉስ 1 ሪቻርድ በሳላዲን ላይ በአርሱፍ ውግያ አሸነፈ።
- 1442 - በቱሙ ምሽግ ውግያ የሞንጎል ሃያላት የቻይናን ንጉስ ማረኩ።
- 1506 - የስኮትላንድ ንጉስ 4 ጄምስ እንግሊዝ ወርሮ በፍሎደን ሜዳ ውግያ ሞቶ ተሸነፈ።
- 1890 - የዳግማዊ ምኒልክ ሻለቆች የካፋን ንጉስ ጋኪ ሸሮቾ በማማረክ ያንን መንግስት ጨረሱ።
- 1935 - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪካን ስትቀርብ በጀርመኖች ተተኩሳ ሰጠመች።
- 1970 - የጸረ-አፓርትሃይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
- 1972 - ነጻነት ለቨንዳ ተሰጠ - ይህ ግን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ አልተቀበለም።
- 1985 - መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች።