ስሜን ሳሚኛ
ከWikipedia
ስሜን ሳሚኛ (davvisámegiella) በኖርዌ ስዊድንና ፊንላንድ የሚናገር ቋንቋ ነው። ከ15,000 እስከ 25,000 ሰዎች ይችሉታል። የሚጻፈው በላቲን ፊደል ነው።
[ለማስተካከል] ተውላጠ ስም
ተውላጠ ስም በሦስት ቁጥር ይካፈላል እነርሱም ነጠላ ሁለትዮሽና ብዙ ናቸው።
አማርኛ | ሳቢ | አማርኛ | አገናዛቢ | |
---|---|---|---|---|
1ኛ (ነጠላ) | እኔ | mun ሙን | የኔ | mu ሙ |
2ኛ (ነጠላ) | አንተ / አንቺ | don ዶን | ያንተ / ያንቺ | du ዱ |
3ኛ (ነጠላ) | እሱ / እሷ | son ሶን | የሱ / የሷ | su ሱ |
1ኛ (ሁለትዮሽ) | እኛ (ሁለታችን) | moai ሞዋይ | የኛ | munno ሙኖ |
2ኛ (ሁለትዮሽ) | እናንተ | doai ዶዋይ | your | dudno ዱድኖ |
3ኛ (ሁለትዮሽ) | ሁለቱ | soai ሶዋይ | የሁለቱ | sudno ሱድኖ |
1ኛ (ብዙ) | እኛ | mii ሚዒ | የኛ | min ሚን |
2ኛ (ብዙ) | እናንተ | dii ዲዒ | የናንተ | din ዲን |
3ኛ (ብዙ) | እነሱ | sii ሲዒ | የነሱ | sin ሲን |