ቭላንደርኛ (Vlaemsch) የሆላንድኛ ቀበሌኛ ነው። በተለይ የሚናገርበት በቤልጅግ ሲሆን ስፍራው በትንሽ ጎረቤት ክፍል ከሆላንድና ከፈረንሣይ ይሸፍናል። በቤልጅግ ውስጥ 1.05 ሚሊዮን፤ በሆላንድም 90,000፤ በፈረንሣይም 20,000 ተናጋሪዎች አሉት።
ቭላንደርኛ በምዕራብ ቭላንደርኛ እና በምሥራቅ ቭላንደርኛ ቀበሌኞች ይለያል።