ነሐሴ 26
ከWikipedia
ነሐሴ 26 ቀን: የሕገመንግስት ቀን በስሎቫኪያ...
[ለማስተካከል] ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- 1513 - ቱርኮች ቤልግራድን ማረኩ።
- 1518 - ቱርኮች በአለቃቸው ሱልጣን ሱለይማን ተመርተው በሞሃች ውጊያ ሀንጋሪ ላይ አሸነፉ።
- 1533 - ቱርኮች ቡዳፐስትን ማረኩ።
- 1856 - በአሜሪካ መነጣጠል ጦርነት የስሜን (ፌዴራሎች) ሠራዊት በአትላንታ ላይ አደጋ ጣለ።
- 1878 - ከምድር መንቀጥቀጥ በሳውስ ካሮላይና 100 ሰዎች ሞቱ።
- 1897 - በካናዳ ውስጥ አልቤርታና ሳስካቸዋን አዳዲስ ግዝቶች ሆኑ።
- 1915 - ታላቅ ምድር መንቀጥቀጥ በጃፓን መቶ ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ገደለ።
- 1931 - አዶልፍ ሂትለር ፖሎኝን በመውረሩ ሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት ጀመረ።
- 1961 - መንፈቅለ መንግስት በሊቢያ ሙአማር ጋዳፊን ከፍ አደረገው።
- 1975 - የኮሪያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሶቭየት ኅብረት ላይ ሲተኮስ 269 መንገደኞች ሞቱ።
- 1983 - ዑዝበክስታን ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።