ኑዋክሾት
ከWikipedia
ኑዋክሾት (ዓረብኛ፦ نواكشوط ወይም انواكشوط) የሞሪታኒያ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ (1991 ዓ.ም.) 881,400 ሆኖ ተገመተ። ከተማው 01°09′ ሰሜን ኬክሮስ እና 15°58′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል። እስከ 1950 ዓ.ም. ድረስ ትንሽ የአሣ አጥማጅ መንደር ብቻ ነበር። ከዚያ እንደ ዋና ከተማ ተመረጠ። ዛሬ የአገሩ 1ኛ ታላቅ ከተማ ነው። ስሙ ኑዋክሾት ከበርበርኛ 'ናዋክሹጥ' (ማለት፣ የንፋሶች ቦታ) እንደ ተወሰደ ይታመናል።