Cookie Policy Terms and Conditions Wikipedia - ናምሩድ

ናምሩድ

ከWikipedia

በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም በአፈ ታሪክናምሩድ (ዕብራይስጥ נִמְרוֹד /ኒምሮድ/) የኩሽ ልጅ፣ የካም ልጅ ልጅ እና የኖህ ልጅ-ልጅ-ልጅ ሲሆን የሜስጶጦምያ ንጉሥና 'በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ' ይባላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስሙ የሚገኘው በኦሪት ዘፍጥረጥ 10፣ በዜና መዋዕልና በትንቢተ ሚክያስ ብቻ ነው። እነዚህ መጻሕፍት ስለ ናምሩድ ብዙ ባይነገሩንም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ስለሱ ያሉት ትውፊቶች ግን በርካታ ናቸው። ከነዚህም ትውፊቶች መካከል ከሁሉ የታወቀው የባቢሎን ግንብ እንዲገነባ ያዘዘ መሆኑ ነው።

ይዞታ

[ለማስተካከል] በመጽሐፍ ቅዱስ

  • ኦሪት ዘፍጥረት 10፡8-10፦
«ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ። እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፦ በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክአርካድ፥ ካልኔ ናቸው።»

መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 1፡10 ከዚህ በላይ ምንም አይጨምርም። ትንቢተ ሚክያስም 5፡6፦ «የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ» ያለው ነው።

በእብራይስጥ ትርጉም ኦሪት ዘፍጥረት 10፡11-12 ዘንድ ነነዌንና በነነዌ ዙሪያ ሌሎች ከተሞች የሠራው የሴም ልጅ አሦር ወይም ናምሩድ መሆኑ ግልጽ አይደለም። ስለዚህ በአንዳንድ ትርጉም ዘንድ በአሦር አገር ያሉትን ከተሞች የሠራው ደግሞ ናምሩድ ነበረ።

በመጽሐፈ ኩፋሌ 8፡39 የኤቦር ሚስት አዙራድ «የአብሮድ ልጅ ናት» ሲል በግሪኩ ደግሞ በ«አብሮድ» ፈንታ «ነብሮድ» አለው፤ ይህም በግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ «ናምሩድ» ማለት ነው። ናምሩድ የኤቦር አማትና የፋሌክ ቅድማያት ከሆነ፣ እንግዲህ አብርሃምና አይሁዶች ሁሉ ኢየሱስ ቢሆንም ከናምሩድ ከኩሽና ከካም ትንሽ ተወላጅነት አለባቸው ማለት ነው።

[ለማስተካከል] በአፈ ታሪክና ትውፊቶች

በአይሁድ ልማዶች ዘንድ የናምሩድ እናት ከምጽራይም ነበረች።

በ1ኛ ክፍለ-ዘመን የአይሁድ ታሪከኛ ፍላቪዩስ ዮሴፉስ ስለ ናምሩድ እንዲህ ብሎ ጻፈ፦

«እግዚአብሔርን ለመናቅና ለማቃለል ያበረታታቸው ናምሩድ ነበረ። እሱ የካም ልጅ ልጅ፣ ደፋር ሰው ነበረ፤ ታላቅ የእጅ ብርታትም ነበረው። ደስታቸው በእግዚአብሔር አማካይነት የደረሠ ሳይሆን ከገዛ ድፍረታቸው የተነሣ እንዲደሰቱ አሳመናቸው። ከዚህ በላይ ቀስ በቀስ መንግሥቱን ወደ አምባገነንነት ቀየረ፤ ሰዎችን ከአምላክ ፍርሃት ለማዛወርና ለራሱ ስልጣን ምንጊዜ ጥገኛ እንዲሆኑ ከማድረግ በቀር ሌላ ዘዴ አላወቀም ነበርና…

ብዙዎቹም የናምሩድን ውሳኔ እንዲከተሉ፣ ለእግዚአብሔርም መገዛት እንደ ቦቅቧቃነት እንዲቆጠሩ በጣም ተዘጋጁ። ግንብም ሠሩ፤ ምንም ጣር አላስቀሩም ወይም በምንም ረገድ ስራቸውን ቸል አላሉም። በስራው ላይ በተደረጉ እጆች ብዛት ምክንያት፣ ማንም ሳይጠብቀው ቶሎ ቶሎ እጅግ ከፍ ከፍ አለ፤ ሆኖም ውፍረቱ በጣም ግዙፍ በመሆኑ፣ ታላቅ ከፍታው ከርቀት ሲታይ ከእውኑ ያነሰው ይመስል ነበር። ውኃ እንዳይዘልቀው የተሠራው በዝፍት ከተመረገ ከተቃጠለ ጡብ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ ያለ አእምሮ እንደ አደረጉ ባየ ጊዜ፣ በሙሉ እንዲያጠፋቸው አላሰበም፤ በቀድሞ ሐጢአተኞች ጥፋት ጥበበኛ አልሆኑምና፤ ነገር ግን ትርምስ አደረገባቸው፣ የተለያዩም ልሣናት አስገኘባቸው፣ በቋንቋዎች ብዛት ሳቢያ እርስ በርስ እንዳይግባቡ። ግንቡን ያገነቡበት ሥፍራ አሁን ባቢሎን ይባላል፤ ምክንያቱም አስቀድሞ በቀላል የገባቸው ቋንቋ ተደናገረና፤ አይሁዶች 'ባቤል' በሚለው ቃል 'ድብልቅ' ማለታቸው ነውና…»

ኪታብ አል-ማጋል የተባለው ጥንታዊ አረብኛ መጽሐፍ (ከ'ቄሌምንጦስ መጻሕፍት' መሃል) እንደሚለው፤ ናምሩድ ሐዳኒዩንን፣ እላሳርን፣ ሴለውቅያን፣ ክቴሲፎን፣ ሩሂን፣ አትራፓተነን፣ ተላሎንንና ሌሎችን ከተሞች ሠራ። የፋሌቅ ዕድሜ 50 አመት ሲሆን ናምሩድ ኒሲቢስን፣ ራሃን (ኤደሣ) እና ካራንን ሠርቶ ከዚህ በላይ የራግው ዕድሜ 163 አመት በሆነበት ወቅት ናምሩድ የዓለም ንጉስ ሆኖ ለ69 አመታት ነገሠ። በተጨማሪ ናምሩድ 'ጥቁር ጨርቅና ዘወድ በሰማይ አይቶ ሸማኔውን ሳሳንን ጠርቶ እሱ በእንቁ ሠሮቶት በራሱ ላይ ጫነው። እሱ መጀመርያ ዘውድ የጫነው ንጉስ ነበረ። ስለዚህ ነገር ምንም የማያውቁ ሰዎች ዘውድ ከሰማይ ወረደለት አሉ።' በኋላ መጽሐፉ ናምሩድ የእሳትና የጣኦት አምልኮት መሠርቶ ለ3 አመት የአስማት ትምህርት ከኖህ 4ኛ ልጅ ከ'ቡኒተር' እንደ ተቀበለ ይላል[1]

በጽርዕ የተጻፈው የመዝገቦች ዋሻ (350 ዓ.ም.) ስለ ናምሩድ ተመሳሳይ ታሪክ አለው፤ ነገር ግን ናምሩድ ኒሲቢስን፣ ኤደሣንና ካራንን የሠራው የራግው ዕድሜ 50 አመት ሲሆን ነው፤ የናምሩድም ዘመን የጀመረው የራግው ዕድሜ 130 በሆነበት ወቅት ይባላል። በዚህ መጽሐፍ ደግሞ የሸማኔው ስም 'ሲሳን'፣ የኖህም አራተኛ ልጅ ስም 'ዮንቶን' ይባላል።

ቅዱስ ሄሮኒሙስ 380 ዓ.ም. ገዳማ በጻፉት ጽሕፈት እብራይስጥ ጥያቄዎች ስለ ኦሪት ዘፍጥረት እንደሚሉ፣ ናምሩድ በባቤል ከነገሠ በኋላ «ደግሞ የነገሠባቸው በኦሬክ እሱም ኤደሣ፤ በአርካድ እሱም አሁን ኒሲቢስ፣ በሐላኔ [ካልኔ] እሱም ስሙ ከተቀየረ በኋላ ስለ ንጉስ ሴሌውቆስ 'ሴሌውቅያ' አሁንም እንዲያውም 'ክተሲፎን' የሚባሉ ከተሞች ናቸው» ነገር ግን ይህ ልማዳዊ መታወቂያ በዘመናዊ ሊቃውንት አይቀበለም፤ የናምሩድ ከተሞች በሶርያ ሳይሆኑ ሁላቸው በሱመር ይገኛሉ ባዮች ናቸውና።

ግዕዝ የተጻፈው መጽሐፈ አዳምና ሕይዋን (ምናልባት ከ5ኛ ክፍለዘመን የታወቀ) ደግሞ ለመዝገቦች ዋሻ ተመሳሳይ ታሪክ አለው፤ በዚህ ግን የዘውዱ ሠሪ ስም 'ሳንጣል'፤ ናምሩድንም ያስተማረው የኖህ 4ኛ ልጅ ስም 'ባርውን' ይባላል።

በ9ኛ መቶ ዘመን 'የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ' የጻፉት የእስላም ታሪከኛ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ ይህን የመሰለ ተረት ያቀርባል ። በዚህ መሠረት ናምሩድ ግንቡን በባቢል (ባቢሎን) አስገንቦ አላህ አጠፋውና የሰው ልጅ ቋንቋ ከዚያ ቀድሞ የሶርያ (አራማያ) ሲሆን የዛኔ ወደ 72 ልሣናት ይደባለቃል። ከዚያ በላይ ደግሞ በ13ኛ መቶ ዘመን የጻፉት ሌላ የእስላም ታሪከኛ አቡ አል-ፊዳ ይህን መሰል ታሪክ ሲያወራ የአብርሃም ቅድመ-አያት ዔቦር ግንቡን ለመሥራት እምቢ ስላለ የፊተኛው ቋንቋ ዕብራይስጥ እንዲቀርለት ተፈቀደ ብሎ ይጽፋል።

በአንዳንድ ምንጭ መሠረት ናምሩድ በግፍ እንደተገደለ ይባላል። ለምሳሌ ከ1618 ዓ.ም. ጀምሮ ብቻ በሚታወቀው «ያሻር መጽሐፍ» በሚባለው የአይሁድ ሚድራሽ ዘንድ፣ ናምሩድ አምራፌል (ዘፍ. 14፡1) ሆኖ የአብርሃም ልጅ ልጅ ዔሳው ራሱን ሰየፈው።

ሀንጋሪ አፈ ታሪክ ደግሞ የሀንጋሪ ሰዎች አባቶች ወንድማማች 'ሁኖር' እና 'ማጎር' ሲሆኑ እነኚህ የታና ልጅ መንሮጥ እና የሚስቱ የኤነሕ መንታዎች ይባላሉ። በአንዳንድ ትውፊት ይህ መንሮጥ የኩሽ ልጅ ናምሩድ እንደ ነበር ይባላል። ጥቂት ደራሲዎች የ'ታና' እና የ'ኩሽ' ስሞች ከታሪካዊ ሱመራዊ የኪሽ ንጉሥ ኤታና ጋር እንዲሁም ከኩሻን መንግሥት (እስኩቴስ) አባት 'ኩሽ-ታና' ጋር ያለውን ተመሳሳይነት አጠቁመዋል። ሆኖም በአንድ መጽሐፍ ዘንድ የሁኖርና የማጎር አባት የኤነሕም ባል ናምሩድ ሳይሆን የኖህ ልጅ ያፌት ነበረ።

በአርሜኒያ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ የአርሜኒያ ሕዝብ መስራች ሐይክ ናምሩድን በቫን ሐይቅ አጠገብ በተካሔደ ፍልሚያ አሸንፎት ነበር።

ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው በሞርሞን ሃይማኖት መጻሕፍት ዘንድ፣ ልሣናት በተደባለቁበት ጊዜ የ'ያሬድ' ወገኖች መጀመርያውን ቋንቋ ጠብቀው በስሜን ቅርብ ወደ ሆነ፣ ስለ አዳኙም 'ናምሩድ' ወደ ተባለ ሸለቆ እንዲጓዙ ታዘዘ።

[ለማስተካከል] ክፉ ናምሩድና ጻድቁ አብርሃም

በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ናምሩድና አብርሃም ምንም ግንኙነት የለም። እንዲያውም ከሁለቱ መካከል 7 ትውልዶች አሉ። ይሁንና የኋለኛ ዘመን አይሁዶች ልማድ ናምሩድና አብርሃም በአንድ ጊዜ የኖሩ ጠላቶች ያደርጋቸዋል። ይህ ልማድ በሐሣዊ ፊሎ ጽሕፈት[2]; በተልሙድም፣ በመካከለና ዘመን ረቢዎች ጽሕፈቶች[3] እና ዛሬም ቢሆን ይገኛል። በናምሩድና በኢብራሂም (አብርሃም) መሃል ያለው ክርክር ደግሞ በእስልምና ቁርዓን ይገኛል። በነዚህ ትውፊቶች አብርሃም ናምሩድን ስለ ጣኦት አምልኮት ይገሥጸዋል። ናምሩድ የፈላጭ ቁራጭና የክፋት አራያ ሆኖ በእብራይስጥ 'ናምሩድ ክፉው' (נמרוד הרשע) በአረብኛም 'ናምሩድ አል-ጃባር' (አምባገነን) ይሠየማል።

[ለማስተካከል] ሌሎች አስተያየቶች

በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ባይነገርም፣ ከጥንት ጀምሮ ናምሩድ የባቢሎንን ግንብ እንዲሠራ ያዘዘው መሪ መሆኑ ተቆጥረዋል። የግዛቱ መጀመርያ በሰናዖር ያሉት ከተሞች ባቢሎንም ስለ ህነ ነው።

ኦሪት ዘፍጥረት 'እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ' ይህ አባባል ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ አመጽ እንዳደረገ እንደ ማለት ይቆጠራል። እግዚአብሔር የምድር ትክክለኛ መሪ ሆኖ ናምሩድ መጀመርያ የሰው ልጅ መንግሥት ስለ ፈጠረ በማለት ነው።

በሊቅ ዴቪድ ሮህል አስተሳሰብ የኡሩክ መስራች ኤንመርካር እና ናምሩድ መታወቂያ አንድ ነው። በጥንታዊ ጽሑፍ ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ መሠረት ኤንመርካር የግንብ መቅደስ በኡሩክ (ኦሬክ) እና በኤሪዱ (ባቢሎን እንደመሰለው) ሠርተው ነበር።

ሌሎች ሊቃውንት ለናምሩድ የተለያዩ መታወቂያዎች አቅርበዋል። የ4ኛ ሮማ ፓፓ ቅሌምንጦስ በጻፉት ደብዳቤ መሠረት ናምሩድ የፋርስ ሃይማኖት ሰባኪ ዛርጡሽት ነበረ [4]። ደግሞ የባቢሎን አምላክ ሜሮዳክ አፈ ታሪክ ከናምሩድ ሕይወት እንደ ተወሰደ ተብሎ ያውቃል። ሌሎች ሃሣብ ናምሩድ በዕውኑ የአሦር ንጉሥ 1ኛ ቱኩልቲ-ኒኑርታ [5] ነበር ይላል. አሌክሳንድር ሂስሎፕ በ19ኛ ክፍለ ዘመን የጻፈው በግሪክ አፈ ታሪክ ዘንድ የሜስጶጦምያ ንጉስና የሴሚራሚስ ባል ኒኑስ ተመሳሳይነት አየ። በመጨረሻ በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር የአካድ መስራች 1ኛ ሳርጎን ስለሆነ አንድ ሃልዮ ናምሩድን ያደርገዋል። ነገር ግን ሌሎች ጽሕፈቶች አካድ ከሳርጎን አስቀድሞ እንደ ነበር ስለሚመሰክር ይህ ሃሳብ ተጠይቋል። አንዳንድ ጥንታዊ ጽሕፈት ደግሞ 1 ሳርጎን ባቢሎንን ወደ አካድ ዙሪያ እንዳዛወረው ይላል።

[ለማስተካከል] ዋቢ ምንጮች

  • The Legacy of Mesopotamia; Stephanie Dalley et al. (Oxford, Oxford University Press, 1998)
  • Noah's Curse: The Biblical Justification of American Slavery; Stephen R. Haynes (NY, Oxford University Press, 2002)
  • "Nimrod before and after the Bible" K. van der Toorn; P. W. van der Horst, The Harvard Theological Review, Vol. 83, No. 1. (Jan., 1990), pp. 1-29
  1. ኪታብ አል-ማጋል (በእንግሊዝኛ ትርጉም)
  2. van der Toorn and van der Horst 1990, p. 19
  3. [1]
  4. Homily IX
  5. Dalley et al., 1998, p. 67

[ለማስተካከል] የውጭ መያያዣዎች

Static Wikipedia 2008 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2007 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2006 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu