እንጦጦ የአዲስ አበባ ከፍተኛ ቦታ ነው። ዳግማዊ ምኒሊክ አዲስ አበባን ሲቆረቁሩ ከአንኮበር መጥተው ያረፉበት እና ቤተ መንግስታቸውን የስሩበት ታሪካዊ ቦታም ነው። እንጦጦ የእንጦጦ ሰንሰለታማ ተራራ አንዱ ክፍል ሲሆን ርዝመቱ ከባህር ወለል በላይ 3200 ሜትር ይደርሳል።