ጃቫ (java)
ከWikipedia
ጃቫ ስነ ፍርገማ በቅርብ ታዋቂነትንና ተቃባይነትን እያገኘ ከመጡ ፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ጃቫ ተመራጭ ካደረጉት ዋና ባሀሪዎቹ አንዱ በፕላት ፎርም አለመወሰኑ ነው። ይሀም ማለት በጃቫ የተጻፈ ትግበራ(አፕሊኬሽን) የጃቫ ቨርቹአል ማሽን ባለበት ሁሉ መሮጥ መቻሉ ነው። ስለዚህ በጃቫ ስራአት የሚጻፍ ኮድ በመጀመሪያ ኮምፓይል ከተደረገ በኋላ ኮምፓይለርኡ አዲስ ዶክመንት ይፈጥራል። ይህም ማለት ኮምፓይለሩ የሚፈጥረው አዲስ ዶክመንት በጃቫ ባይት ኮድ ሲሆን የሚተገበረው(ኢምፕልመንት የሚደረገው) በያቫ ቨርቹዋል ማሽን ነው። እናም ጃቫን ከለሌሎቹ የሚለየው ምንም አይነት ቁስ ሳይጨመር ሌላ ማሽን በመጠቀም ፋንታ በሶፍት ዌር ብቻ መስራት መቻሉ ነው። ስለዚህ የሶፍት ዌሩ ስም ጃቫ ቨርቹአል ማሽን ነው።
[ለማስተካከል] ጃቫን ኢንስትቶል ስለ ማድረግ
ጃቫን ለመምረጥ ሌላው ዋናው ምክንያት በነጻ መገኘቱ ነው። ስለሆነም ጃቫን ከሚከተለው ሊንክ ላይ ዳውንሎድ ማድረግ ይቻላል፤ http://java.sun.com/javase/downloads/index.jsp ጃቫን ኢንስቶል ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ መሳሪያ(ኢንቲግሬትድ ዴቨሎፕመንት ቱል) መጠቀም ይቻላል። ይህም በኮማንድ ላይን ከመጠቀም የቀለለ ነው። ይሁን እንጂ ብዙ አይነት አይ.ዲ.ኢ.(IDE) ስላለ የእያንዳንዱ አጠቃቀም ከሌላው አይነት ይለያል። በብዛት የሚታወቀው አይ.ዲ.ኢ ኔትቢንስ 5.5 ይባላል። ኔትቢንስን ከሚከተለው ሊንክ ላይ ማግኘት ይቻላል፤ http://www.netbeans.org/downloads/
[ለማስተካከል] የጃቫ ምስጢር
በእጅ ታይፕ በማድረግ የጃቫን ጥሬ ኮድ ፋይል ካስገባን በኋላ ጥሬ ኮዱን በጃቫ ኮምፓይለር ኮምፓይል ይደረጋል፤ይህም ማለት በእጅ የተጻፈው ምንጭ ኮድ ከስህተት ነጻ መሆኑንና ለማሽን በሚገባ ቋንቋ በትክክል መተርጎሙን ማረጋገጥ ነው። ኮምፓይል የተደረገው ባይትኮድ በማንኛውም ጃቫ ቨርቹአል ማሽን ላይ መሮጥ ይችላል።
[ለማስተካከል] የኮድ መዋቅር በጃቫ
የጃቫ ምንጭ ኮድ በ HelloWorld.java መልክ መቀመጥ ይኖርበታል። ይህም የጃቫ ምንጭ ፋይል ነው። በጃቫ ምንጭ ፋይል ውስጥ ክላስ ይቀመጣል። ክላስ የፕሮግራሙን ቁራጭ ያመለክታል።ወይም አንድ ክላስ ብቻውን ፕሮግራም ሊሆን ይችላል። HelloWorld የሚለው ቃል በተጠቀሰው ምንጭ ፋይል ውስጥ (ማለትም በ HelloWorld.java ውስጥ) የክላሱን ስም ያመለክታል። በክላስ ውስጥ ሜተድ(method) የሚባል ነገር ይቀመጣል። አንድ ክላስ ብዙ ሜተዶች ሊኖሩት ይችላሉ። በሜተድ ውስጥ ስቴትመንቶች ይቀመጣሉ ማለት ነው።