From Wikipedia
- ወደ ዊኪፔድያ እንኳን ደኅና መጡ!
ዊኪፔድያ የተሟላ፣ ትክክለኛ እና፡ ነጻ መዝገበ ዕውቀትን በብዙ ቋንቋዎች ለማቅረብ የሚጥር የትብብር ሥራ ውጤት ነው። ይህ የአማርኛው ዊኪፒዲያ ጥር 18 ቀን 1996 ዓመተ ምሕረት (27 January 2004 እ.ኤ.አ.) የተጀመረ ሲሆን 2,896፡ ጽሑፎችን፡ አካቶ ይዟል።
ይህን መዝገበ እውቀት የተሟላ ለማድረግ አሁን ካሉት መጣጥፎች በብዙ ዕጥፍ የሚበልጡ ጽሑፎች ያስፈልጉናል። ስለ ማንኛውም ነገር ዕውቀት ያላቸው ሰዎች በተለያዩ ርእሶች መጣጥፍ በማዘጋጀት እየተሳተፉ ነው። እባክዎን እርስዎም በአማርኛ መጻፍ ከቻሉ፣ በሚፈልጉት ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ ጽሑፎችን በማቅረብ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት አስተዋጽኦ ያድርጉ። ይህ ሥራ ወደፊት በጣም ትልቅና ጠቃሚ የዕውቀት ምንጭ እንደሚሆን ተስፋ አለን።
ዊኪፔድያ የጋራ ነው። ማንኛውም ሰው ለዚህ መዝገበ ዕውቀት ተዋጽዖ ሊያደርግ በነፃ ይችላል። ጽሑፍ ለማቅረብ ወይም በአርትዖት ሥራ ለመሳተፍ ዘዴው በጣም ቀላል ነው። ጽሑፍ ለማቅረብም ሆነ የጽሑፍን ስሕተት፣ የፊደል ግድፈት (ታይፖ)፣ ወዘተ. ለማስተካከል፤ ወይም የጽሑፍ ማከያ ለማቅረብ ማድረግ ያለብዎት በዚያው ገጽ የኅዳግ ጥግ ያለውን "ይህን ገጽ ለማዘጋጀት" የሚለውን መጫን ብቻ ነው።
- ለጀማሪዎች የዊኪፔድያ ቀላል መማርያ እዚህ ያገኙ።
በቀይ ቀለም የሚታዩ ቃላት ገና ያልተጻፉ አርእስትን ይጠቍማሉ። በእነዚህም ሆነ በሌሎች ርእሶች ላይ አዲስ መጣጥፍ ለማቅረብ ይችላሉ። ሥራዎ ያልተጠናቀቀ መስሎ ቢሰማዎ እምብዛም አይጨነቁ፤ አንዳችን የሌላችንን ስራ (ጽሑፍ) በማረም በጋራ በጣም ጠቃሚ መጣጥፎችን ማበርከት እንችላለን።
በተጨማሪ የእርዳታ ገጽ ላይ የቀረበውን ማስታወሻ አንብበው ማንኛዉንም ጽሑፍ ለማቅረብ ከአሁን ጀምሮ ይሞክሩ። ሙከራ ለማድረግ ቢፈልጉ፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ መፈተኛው ቦታ መሻገር ይችላሉ።
የተሳትፎዎትን መጀመርያ መጣጥፍ ከእንግሊዝኛው ዊኪፔድያ በመተርጐም ማቅረብ ይቀልዎት ይሆናል። እጅግ ብዙ ትርጕም መጣጥፎች ቢኖሩን ለአማርኛው ዊኪፒዲያ ማደግ መልካም መንገድ ይጠርጋሉ።
- ዛሬ ሰኞ፣ መጋቢት 17 ቀን 1999 ዓመተ ምኅረት ነው።
- የዛሬ ቀን (እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር) 26 March, 2007 እ.ኤ.አ. ነዉ።
[ለማስተካከል] To download an Amharic unicode font for correct display:
- Please see the font section for more information.
|
- ስለ ምን ለማወቅ ይፈልጉ ነበር? ሀሣብዎን በዚህ ያቅርቡ።
- ቀልዶችን ያውቃሉ? እዚህ ላይ ይጨምሩ!
ምርጥ ፅሑፎች |
-
"ጉግል (Google) በ1998 እ.ኤ.አ. የግለሰብ ድርጅት ሆኖ ነው የጀመረው። የጉግል ፍለጋ ዌብሳይትን የሰራው እና የሚያስተዳድረው ይሄው ድርጅት ነው። የጉግል ዓላማ የዓለምን መረጃ ለማሰናዳት ፣ ለማቅረብና ጠቃሚ ማድረግ ነው።
|
|
|
ዜና እረፍት: |
|
|
ታሪክ በዛሬው ዕለት (March 26, 2007 እ.ኤ.አ.): Wikipedia:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 17 |
|