ሃዲስ አለማየሁ
From Wikipedia
ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ከአባታቸው ከቄስ አለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ አለሙ በደብረ ማርቆስ ወረዳ በእንዶር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በ1902ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት መከታተል ጀመሩ። የቤተክርስቲያን ስርአታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በሗላ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በሗላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ግዜ በአስተማሪነት ሰራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።
በጦር ሜዳ ዘምተው ሲዋጉ ቆይተው በአርበኝነት ሲንቀሳቀሱ በመያዛቸው ጣሊያን ከራስ እመሩ ሀይለ ስላሴ ጋር ተልከው ለሰባት አመት ታስረው ቆይተዋል።
ከዚያም በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በሗላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ግዜ አገልግለዋል።
አዲስ አለማየሁ በርካታ የስነጽሁፍ ስራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ስራቸው ፍቅር እስከ መቃብር በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ያተኩራል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።
ከዚህ ባሻገር:
- የበሻና የወደሁላ ጋብቻ
- ተረት ተረት የመሰረት
- ትዝታ
የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ስራዎች ባለቤት ናቸው።
አዲስ አለማየሁ በ1996ዓ.ም. በ 94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።