ሮቤል ተክለማርያም
From Wikipedia
ሮቤል ተክለማርያም (1966 ዓ.ም. የተወለደ) በ1998 (2006) ዊንተር ኦሊምፒክስ ውስጥ በስኪ ቡድን ኢትዮጵያን የወከለ ነው። በዊንተር ኦሊምፒክስ ጨዋታዎች በማንኛውም ጨዋታ ኢትዮጵያን የወከለው መጀመርያው እስፖርተኛ ነበር።
ከ9 አመት እድሜው ወዲህ በአሜሪካ ውስጥ ምንም ቢኖርም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስኪ ፌዴሬሽን ጀምሮ ይመራል። በአማርኛም እስከ ዛሬ ድረስ አቀላጥፎ ይናገራል።
በውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ካላገዙት በቀር፣ ባለፈው የካቲት በጣልያ ወደ ነበሩ ጨዋታዎች አልደረሰም እንደ ነበር ብሏል። ደግሞ ከገባቸው ከሁለቱ ጨዋታዎች (ተራራማ ስኪ እና ሀገር አቋራጭ ስኪ) አሁን ሽልማት አለማግኘቱ እርግጠኛ እንደ ሆነ ተቀብሏል። «እኔ የተጨባጭ ሁኔታ ሰው ነኝ። ዓላማዎቼ በመንገዱ ላይ ለረጅሙ ነው። ይህ ኦሊምፒክስ ዐይኖቼን በተስፈኝነትም የሌሎችን ኢትዮጵያውያን ዐይኖች እንዲከፍት እፈልጋልሁ።»