አፋር (ክልል)
From Wikipedia
አፋር ክልል (ክልል 2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዋና ከተማው አሳይታ ሲሆን ወደፊት ግን ሰመራ የሚባል አዲስ ከተማ ዋና ከተማው እንዲሆን በሥራ ላይ ነው። 96,707 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 1,188,000 ነው።
የድንቅ ነሽ ወይም ሉሲ አጽም በአፋር ክልል ውስጥ በኅዳር 15 ቀን, 1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.) ነው የተገኘው። በማርች 5, 2005 ደግሞ ሌላ 3.8 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት አጽምም በዚሁ ክልል ተገኝቷል።