ኤንመርካር
From Wikipedia
ኤንመርካር በሳንጋር (ሱመር) ነገስታት ዝርዝር ዘንድ ኡሩክ (ኦሬክ) ከተማ የመሰረተ ነበር፤ በዚያ ዝርዝር ጽህፈት 420 ዓመት እንደ ነገሰ ይላል። ደግሞ አባቱ የኡቱ ልጅ መስኪያግካሸር ወደ ባሕር ገብቶ ኤንመርካር መንግስቱን ከኤያና ከተማ እንዳመጣ ይጨምራል።
የኤንመርካር ስም በሌላ የሳንጋር ጽሑፍ ደግሞ ተገኝቷል። ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ተረት እሱ የኡቱ ልጅ ይባላል። (ኡቱ በሳንጋር እምነት የጸሓይ አምላክ ነበር።) ይህ ተረት የሰው ልጅ ልሳናት መደባለቁን ይናገራል። ኡሩክን ከመመስረቱ በላይ ታላቅ መስጊድ በኤሪዱም እንዳሰራ ይተረታል።
ዴቪድ ሮኅል የሚባል አንድ የታሪክ ሊቅ የኤንመርካርና የናምሩድ ተመሳሳይነት አመልክቷል። "-ካር" የሚለው ክፍለ-ቃል በሳንጋር ቋንቋ ማለት "አዳኝ" ነው። ኡሩክ ከተማ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ነበር ሲባል፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ። በሌላ ትውፊቶች ዘንድ ይህ ናምሩድ የባቢሎን ግንብ መሪ የሆነ ነበር። በተጨማሪም አቶ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም "ባቤል" እንደ ነበር ያምናል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ።