ጉጃራቲ
From Wikipedia
ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው።
[ለማስተካከል] ታሪክ
የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር።
አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
[ለማስተካከል] ምሳሌዎች
የህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ በመሆኑ፣ ጉጃራቲ ለእንግሊዝኛ ሩቅ ዘመድ ይባላል። ስለዚህ ለአንዳንድ ቃል ትንሽ ተመሳሳይነት አላቸው።
- ጉጃራቲ - አማርኛ:
- ሐጥ - እጅ
- ሞዱ - አፍ
- ግር - ቤት
- ሢህ - አንበሳ
- ጊድ - አሞራ
- ኒሻል - ትምርት ቤት
- ናረንጊ - ብርቱካን
- ሊሎ - አረንጓዴ
- ናማስተ - ሰላምታ
- ገም ጮ? - ደህና ነዎት?
- በረቫድ - እረኛ
- አድያፑክ - አስተማሪ
- ዲቨስ - ቀን
- ሞሂኖ - ወር
- ሰቫር - ጧት
- ጋዲ - መኪና