From Wikipedia
[[{{{link}}}| ]]
[[Image:{{{image}}}|14px|{{{link}}}]]
ሜሪላንድ(Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳየንስና የሕክምና ኢንስትቲዩቶች በዚሁ ስቴት ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ2004 እ.ኤ.ኣ. የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መአከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።
የህዝቡ የዘር ክፍልፋይ
- 62.1%-ነጭ
- 27.9%-ጥቁር
- 4.3%-ላቲን
- 4.0%-ኤሲያን
- 0.3%-ቀይ ህንድ
- 2.0%-ክልስ
የሐይማኖት ክፍልይ
- ክርስቲያን-82%
- ፕሮቴስታንት-56%
- ባፕቲስት-18%
- ሜቶዲስት-11%
- ሌላ ፕሮቴስታንት-27%
- ሮማን ካቶሊክ-23%
- ሌላ ክሪስቲያን-3%
- ይሁዳ-3%
- ሌላ ሐይማኖት-15%
- አናፖሊስ - የስቴቱ ዋና ከተማ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ሀይል ማሰልጠኛ የሚገኝበት ቦታ
- ባልቲሞር - በሕዝብ ብዛት ከስቴቱ አንደኛ
- ኮሌጅ ፓርክ - ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ የሚገኝበት ቦታ
- ኮለምቢያ - ከስቴት 2ኛ ትልቅ ከተማ
- ኦሽን ሲቲ - ታዋቂ የባሕር ዳር መዝናኛ (ቢች) ያለበት ሥፍራ
- ሮክቪል - የሞንትጎምሪ ክልል (ካውንቲ) የንግድ ማዕከል
- ሳሊስበሪ - የዴልማርቫ ልሳነ ምድር (ፔኒንሱላ) ትልቁ ከተማ እና የንግድ ማዕከል
- ታውሰን - የባልቲሞር ክልል (ካውንቲ) መንግስት መቀመጫ
[ለማስተካከል] በሜሪላንድ ውስጥ የሚገኙ ክልሎች(ካውንቲዎች)
ካውንቲ |
የተመሠረተበት ዓ.ም.(እ.ኤ.ኣ.) |
የመንግስት መቀመጫ |
አለገኒ ካውንቲ |
1789 |
ከምበርላንድ |
አን አረንዴል ካውንቲ |
1650 |
አናፖሊስ |
ባልቲሞር ካውንቲ |
1659 |
ታውሰን |
ካልቨርት ካውንቲ |
1654 |
ፕሪንስ ፍሬድሪክ |
ካሮላይን ካውንቲ |
1773 |
ዴንተን |
ካሮል ካውንቲ |
1837 |
ዌስትሚንስትር |
ሲሲል ካውንቲ |
1672 |
ኤልክተን |
ቻርልስ ካውንቲ |
1658 |
ላ ፕላታ |
ዶርቸስተር ካውንቲ |
1668 |
ኬምበሪጅ |
ፍሬደሪክ ካውንቲ |
1748 |
ፍሬደሪክ |
ጋሬት ካውንቲ |
1872 |
ኦክላንድ |
ሀርፎርድ ካውንቲ |
1773 |
ቤል ኤር |
ሀዋርድ ካውንቲ |
1851 |
ኤሊኮት ሲቲ |
ኬንት ካውንቲ |
1642 |
ቼስተር ታውን |
ሞንትጎምሪ ካውንቲ |
1776 |
ሮክቪል |
ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ |
1695 |
አፐር ማርልቦሮ |
ክዊን አን ካውንቲ |
1706 |
ሴንተርቪል |
ሴንት ሜሪ ካውንቲ |
1637 |
ለናርድታውን |
ሶመርሰት ካውንቲ |
1666 |
ፕሪንስስ አን |
ታልቦት ካውንቲ |
1662 |
ኢስተን |
ዋሽንግተን ካውንቲ |
1776 |
ሄገርስታውን |
ዊኮሚኮ ካውንቲ |
1867 |
ሳሊስበሪ |
ዎርስተር ካውንቲ |
1742 |
ስኖው ሂል |
[ለማስተካከል] ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች
- ባልቲሞር ኸብሪው ዩኒቨርሲቲ
- ባልቲሞር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
- ካፒቶል ኮሌጅ
- ቼሳፒክ ኮሌጅ
- ኮሌጅ ኦፍ ኖትር ዳም ኦፍ ሜሪላንድ
- ኮለምቢያ ዩኒየን ኮሌጅ
- ጋውቸር ኮሌጅ
- ሁድ ኮሌጅ
- ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ
- ሎዮላ ኮሌጅ
- ሜሪላንድ ኢንስትቲዩት ኮሌጅ ኦፍ አርት
- ማክዳንኤል ኮሌጅ
- ሞንትጎምሪ ኮሌጅ
- ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ
- ማውንት ሴንት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ
- ሴንት ጆንሰ ኮሌጅ
|
- ሴንት ሜሪ ኮሌጅ ኦፍ ሜሪላንድ
- ሶውጆርነር-ዳግላስ ኮሌጅ
- ዩኒፎርምድ ሰርቪስስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዘ ኸልዝ ሳየንስስ
- ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫል አካዳሚ
- ቦዊ ስቴት ዩኒቨርሲቲ
- ኮፒን ስቴት ዩኒቨርሲቲ
- ፍሮስትበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ
- ሳሊስበሪ ዩኒቨርሲቲ
- ታውሰን ዩኒቨርሲቲ
- ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ባልቲሞር
- ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ
- ዩኒቨርሲቲስ አት ሼዲ ግሮቭ
- ዋሽንግተን ባይብል ኮሌጅ
- ዋሽንግተን ኮሌጅ
- ቪላ ጁሊ ኮሌጅ
|