ካቶቪጸ
From Wikipedia
የከተማ አርማ | |
---|---|
ካቶቪጸ (Katowice) (ድምጽ: [ካቶቪጸ]፣ ደግሞ በጀርመንኛ "ካቶቭትዝ" Kattowitz ይባላል) የፖሎኝ ከተማ ነው። ሲሌሲያ በሚባል ታሪካዊ አካባቢ በአገሪቱ ደቡብ በክሎድኒጻ እና በራቫ ወንዞች መካከል ይገኛል። 315,123 ያሕል ሰዎች ይኖሩበታል። የከተማው ከንቲባ ፕዮትር ኡሦክ ናቸው።
የከደል ማዕድንና የብረታብረት ሥራ መኻል ነው። ዘመናዊ እና የቆዩ ሕንጻዎችና አንድ ትንሽ የአውሮፕላን ማረፊያ አለው።
የከተማነት ሁኔታ በሕግ የተቀበለው በ1857 ዓ.ም. ነበር። ሲሌሲያ ለረጅም ጊዜ የጀርመን ክፍላገር ሆኖ ከተማው እስከ 1910 ድረስ በጀርመን ውስጥ ይገዛ ነበር።
ከ1946 ዓ.ም. እስከ 1948 ድረስ የካቶቪጸ ስያሜ "ስታሊኖግሮድ" ማለት "የስታሊን ከተማ" ነበር። ይህ ስም የተሰጠው በኮሙኒስቶች ወገን ነው።
ይዞታ |
[ለማስተካከል] ቀበሌዎች
I. ከተማ
II. ስሜን መንደር
III. ምዕራብ መንደር
|
IV. ምሥራቅ መንደር
V. ደቡብ መንደር
|
[ለማስተካከል] ካቶቪጸ ታዋቂ ኗሪዎች
- ሃንስ ቤልመር, የፎቶ አንሺ
- ኸንሪክ ብሮደር, ጋዜጠኛ
- ማሪያ ጉፐርት-ማየር
- ኩርት ጎልድስታይን የነርቭ ሃኪም
- ጀርዚ ኩኩችካ
- ካዚሚርዝ ኩትዝ
- ፍራንዝ ሌዮፖልድ ኖይማን
- ሃንስ ሳክስ