የጥንተ፡ንጥር ጥናት (ኬሚስትሪ)
From Wikipedia
ኬሚስትሪ ወይም የጥንተ-ንጥር ጥናት የቁሶችን አሰራር እና ጸባይ ያጠናል።
የ"ኬሚስትሪ" ስም የሚመጣ ከእንግሊዝኛ ሲሆን እሱ የተወለደ ከ1700 በፊት "አልኬሚ" ከተባለ ሌላ ጥናት ነበር። ይህም አልኬሚ ዋና ዒላማ ብረት ወደ ወርቅ ለመቀየር ነበር። የማይቻል ምኞት እንደ ነበር የዛኔ ተገነዘበ። አልኬሚ የሠራ ሰው 'አልኬሚስት' ተባለ ወይም በአጭሩ 'ኬሚስት'። በኋላ ትውልድ የኬሚስት ሥራ 'ኬሚስትሪ' ተባለ።
የ"አልኬሚ" ስም ደግሞ የወጣ ከዓረብኛ "አል-ኪሚያ" (الكيمياء ወይም الخيمياء) ማለት "የመቀየር ጥበብ" ሲሆን የዚህ ቃል መነሻ እርግጠኛ አይደለም። ወይም ከግሪክ "ቄሜያ" (χημεία, ቀላጭ ብረታብረት) ወይም ከግብጽ ዱሮ ስም "ከመት" ("የከመት ጥበብ" ለማለት) ሊሆን ይችላል።