የመሬት ጥናት ወይም ጂዮሎጂ (ከግሪክ γη- ጌ፣ ምድር እና λογος ሎጎስ፣ ቃል፥ ጥናት) ስሙ እንደሚያመለክተው የመሬትን አሠራር፣ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎችን እና ታሪክ ያጠናል። ይህ ጥናት የመሬትን ውስጣዊ አሰራር አንድንገነዘብ በጣም ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። ይህ ሙያ የተፈጥሮ ሐብቶችም የሚገኙበትን ቦታ እንድናውቅ ይረዳናል።