ከWikipedia
ሳንስክሪት ጥንታዊ የሕንድ ቋንቋ ነበር። ለሕንዱ ለቡዳ እና ለጃይን ሃይማኖቶች እንደ ቅዱስ ቋንቋ ተቆጠረ። ብዙ ዘመናዊ ቋንቋዎች እንደ ህንዲ ማራጢ ወዘተ. የወጡ ከሳንስክሪት ነው። በዚህ ረገድ እንደ ሮማይስጥ ለአውሮጳ ወይም እንደ ግዕዝ ለኢትዮጵያ የሚመስል ሁናቴ አለው። እስከ ዛሬም ድረስ ከሕንድ 22 ይፋዊ ቋንቋዎች ውስጥ ይገኛል።
በብዙ አይነት ፈደሎች ሊጻፍ ይቻላል።
አጠራር:
ሺቮ ርክሽቱ ጊርቫንባሻርሳስቫድትትፕራን።
ትርጉም:
«በአማልክት ቋንቋ ደስ ያሉትን ሺቫ ይባረካቸው።»
-