ኮርንኛ
ከWikipedia
- ይህ መጣጥፍ በብሪታንያ ስለሚገኘው ቋንቋ ነው። በእስያ ለሚገኘው ቋንቋ ለመረዳት፥ ኮሪይኛ ይመለከቱ።
ኮርንኛ (Kernewek, Kernowek, Curnoack) በእንግሊዝ የሚናገር ቋንቋ ነው። በኬልቲክ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሆኖ የብረቶንኛና የዌልስኛ ቅርብ ዘመድ ነው።
የሚናገረው በእንግሊዝ አገር ደቡብ-ምዕራብ ጫፍ ወይም ኮርንዋል ነው። ቀደም ሲል ይህ ቋንቋ ከ1800 ዓ.ም. በፊት ጠፍቶ ነበር። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ግን ስለ ቋንቋው አዲስ ትኩረት ተገኝቶ አሁን እንደ መነጋገርያ ታድሷልና 3,500 የሚያሕሉ ሰዎች ይችሉታል።
በ569 ዓ.ም. ከዴዮርሃም ውግያ ቀጥሎ የደቡብ-ምሥራቅ ብሪታንያ ሕዝቦች በዌልስ ከኖሩት ዘመዶቻቸው በሴያህስ ጀርመናዊ ወገን ተለያዩ። እንግሊዞች መንግሥታቸውን ሲያስፋፉም ብሪታኖች ያሠለጠኑት ግዛት በየጊዜው ይቀነስ ነበር። የኮርንዋል መንግሥት መጨረሻ በ922 ዓ.ም. እንግሊዞች ድል ሲያደርጋቸው ሆነ። ሆኖም ቋንቋቸው ከዚህ በኋላ ይፈራ ጀመር። ዛሬ ሶስት የአጻጻፍ ዘዴዎች አሉት።
[ለማስተካከል] ምሳሌ
አጠራር | ኮርንኛ (ይፋዊ አጻጻፍ) | አማርኛ |
---|---|---|
ከርነወክ | Kernewek | ኮርንኛ |
ግወነነን | gwenenenn | ንብ |
ካዶር | kador | ወንበር |
ከውስ | keus | አይብ |
ኢን-መስ | yn-mes | መውጫ |
ኮድሃ | koedha | መውደቅ |
ጋቨር | gaver | ፍየል |
ቺ | chi | ቤት |
ግወውስ | gweus | ከንፈር |
አበር | aber | አፍ (የወንዝ) |
ኒቨር | niver | ቁጠር |
ስኮል | skol | ትምህርት ቤት |
መጊ | megi | ማጨስ |
ስተረን | sterenn | ኮከብ |
ኸድሂው | hedhyw | ዛሬ |
ህዊባና | hwibana | መፏጨት |
ኮርንኛ | አጠራር | አማርኛ |
---|---|---|
Myttin da | ምትን ዳ | መልካም ጥዋት |
Dydh da | ድዝ ዳ | መልካም ቀን |
Fatla genes? | ፋትላ ገነስ | እንዴት ነህ? |
Yn poynt da, meur ras | 'እን ፖኢንት ዳ, ሜር ራስ | ደህና እግዜር ይመስገን |
Py eur yw hi? | ፒ ኤር ይው ሂ? | ስንት ሰዓት ነው? |
Ple'ma Rysrudh, mar pleg? | ፕሌ ማ ርዝሩዝ, ማር ፕለግ | ርዝሩዝ የት አለ እባክህ? |
Yma Rysrudh ogas dhe Gammbronn, heb mar! | ኢማ ርዝሩዝ ኦጋስ ዘ ጋምብሮን, ኸብ ማር! | ርዝሩዝ ለካምቦርን ቅርብ ነውኮ |