1982
ከWikipedia
1982 አመተ ምኅረት
- መስከረም 1 - "የብረት መጋረጃ" በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ።
- መጋቢት 2 - ሊትዌኒያ ነጻነት ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
- መጋቢት 9 - ምሥራቅ ጀርመን ለመጀመርያ ጊዜ ነጻ ምርጫ አደረገ።
- መጋቢት 12 - ናሚቢያ ከ75 አመታት ግዛት በኋላ ነጻነትዋን ከደቡብ አፍሪካ አገኘች።
- ሰኔ 5 - የሩሲያ ምክር ቤት ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
- ሐምሌ 20 - ቤላሩስ ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
- ነሐሴ 22 - ሳዳም ሁሰይን ኩወይት የኢራቅ ክፍላገር ነው ይላል።
1980ዎቹ: 1980 1981 1982 1983 1984 1985 1986 1987 1988 1989