መስከረም 1
ከWikipedia
መስከረም 1 ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር የመጀመርያው ቀን ነው። በመሆኑም ቁኑ የኢትዮጵያ አዲስ አመት በዓል ነው። በዓሉም እንቁጣጣሽ በመባል ይታወቃል።
ብሄራዊ ቀን በካታሎኒያ እስፓንያ...
[ለማስተካከል] ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- 1507 - የፖሎኝ ሠራዊት በኦርሻ ውግያ በሩስያ ላይ አሸነፈ።
- 1806 - የአሜሪካ መርከቦች በኤሪ ሐይቅ በእንግሊዝ አሸነፉ።
- 1890 - በላቲመር ፔንሲልቬኒያ ፖሊሶች 19 የማዕደን ሰራተኞች በእልቂት ገደሉ።
- 1915 - የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ።
- 1936 - የጀርመን ሃያላት ሙሶሊኒን ከእስር በት እንዲያመልጥ ነጻ አወጡት።
- 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ።
- 1994 - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ተዋጊዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ።