ዓመት በዓላት እና ታሪካዊ ማስታወሻዎች
From Wikipedia
መስከረም 1 ቀን: ዕንቁጣጣሽ፣ ብሄራዊ ቀን በካታሎኒያ እስፓንያ...
[ለማስተካከል] እንኳን 1999 አደረሳችሁ!!!
- 1507 - የፖሎኝ ሠራዊት በኦርሻ ውግያ በሩስያ ላይ አሸነፈ።
- 1806 - የአሜሪካ መርከቦች በኤሪ ሐይቅ በእንግሊዝ አሸነፉ።
- 1890 - በላቲመር ፔንሲልቬኒያ ፖሊሶች 19 የማዕደን ሰራተኞች በእልቂት ገደሉ።
- 1915 - የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ።
- 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ።
- 1994 - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ታጣቂዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ።
መስከረም 2 ቀን: ብሄራዊ ቀን በኬፕ ቨርድ...
- 1184 - በመስቀል ጦርነት የእንግሊዝ ንጉስ 1 ሪቻርድ በሳላዲን ላይ በአርሱፍ ውግያ አሸነፈ።
- 1890 - የዳግማዊ ምኒልክ ሻለቆች የካፋን ንጉስ ጋኪ ሸሮቾ በማማረክ ያንን መንግስት ጨረሱ።
- 1935 - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪካን ስትቀርብ በጀርመኖች ተተኩሳ ሰጠመች።
- 1970 - የጸረ-አፓርትሃይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
- 1972 - ነጻነት ለቨንዳ ተሰጠ - ይህ ግን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ አልተቀበለም።
- 1985 - መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች።
መስከረም 3 ቀን
- 1883 - ሳልስበሪ ሮዴዚያ ተመሰረተች።
- 1893 - በፊሊፒንስ ጦርነት የፊሊፒንስ ተዋጊዎች በአሜሪካ ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ።
- 1899 - በአውሮፓ የተደረገ መጀመርያው የአውሮፕላን በረራ።
- 1907 - በ1ኛ አለማዊ ጦርነት የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች ጀርመን ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ (ናሚቢያ) ወረሩ።
- 1952 - መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ።
- 1996 - ስዊድን በምርጫ ለዩሮ እምቢ አለች።
መስከረም 4 ቀን
- 1534 - ሳንቲያጎ ቺሌ በኗሪ አርበኞች ጠፋ።
- 1676 - የአውሮፓ ሠራዊት በቪኤና ውግያ ቱርኮችን አሸነፉ።
- 1894 - የአሜሪካ ፕሬዚዳን መኪንሊ ተተኩሰው ሲሞቱ ቴዮዶር ሮዝቬልት ፕሬዚዳን ሆኑ።
- 1953 - "ኦፐክ" - የዘይት አስወጪ አገሮች ድርጅት - ተመሰረተ።
...
ነሐሴ 17 ቀን: ነጻነት ቀን በሮማንያ፤ ኡምህላንጋ (የሸምበቆ) በዓል በስዋዚላንድ...
- 1931 - ሂትለርና ስታሊን በሥውር ፊርማ ፖሎኝን አካፈሉ።
- 1954 - መጀመርያ ቴሌቪዥን ግንኙነት በአሜሪካና በአውሮጳ መካከል
- 1958 - መጀመርያ የምድር ፎቶ በጨረቃ ምኋር ካለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር ተነሣ።
ነሐሴ 18 ቀን: የባንዲራ ቀን በላይቤሪያ፤ ብሔራዊ በዓል በዩክራይን፣ ሲዬራ ሌዎን...
- 1825 - ባርነት በእንግሊዝ አገር ግዛቶች ሁሉ ባዋጅ ተከለከለ።
- 1831 - እንግሊዝ ሆንግኮንግን ማረከ።
- 1960 - ፈረንሳይ ንዩክሌር ቦምብ በፈተና በመፈንዳቷ ወደ ንዩክሌር ሃያላት ገባች።
ነሐሴ 19 ቀን: ብሔራዊ በዓል በዩሩጓይና በፊልፒንስ...
- 1791 - ስልጣን ለመያዝ ናፖሌዎን ከግብፅ ወደ ፈረንሳይ ወጣ።
- 1806 - የእንግሊዝ ጭፍሮች በጦርነት ዋሺንግቶን ዲሲ ገብተው ዋይት ሃውስን አቃጠሉ።
- 1850 - በሪችሞንድ ቪርጂኒያ 90 ጥቁሮች ትምህርት ስለተማሩ ታሰሩ።
- 1912 - ፖሎኝ በዋርሳው ውጊያ በሩሲያ ቀይ ጭፍሮች ላይ ያሸነፋል።
- 1936 - ፓሪስ ከተማ በጓደኞች አርበኞች ከጀርመን ነጻ ወጣች።
- 1981 - ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈልክ አለፈ።
ነሐሴ 20 ቀን: ዓመት በአል በናሚቢያ፤ የሱልጣን ልደት በዓል በዛንዚባር...
- 1822 - ቤልጅክ በኔዘርላንድ ላይ አመጸ።
- 1912 - ሴቶች በአሜሪካ ዩናይትድ እስቴት የምርጫ መብት አገኙ።
- 1978 - በመርዝ ጋዝ አደጋ በካሜሩን 1700 ሰዎች ሞቱ።
- 1989 - በእስላም ታጣቂዎች በአልጄሪያ በተገረገ እልቂት 60-100 ሰዎች ተገደሉ።
- 1994 - የምድር ጉባኤ ስብሰባ በጆሃነስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ጀመረ።
- 1564 - ካቶሊኮች በፈረንሳይ ፕሮቴስታንቶች ላይ የበርተሎሜዎስ እልቂት ጀምረው መሪያቸውን ደኮልኒን ገደሉ።
- 1831 - አሚስታድ የተባለ በአፍሪቃውያን የተማረከው መርከብ ወደ ኒው ዮርክ ደረሰ።
- 1875 - ክራካቶአ የተባለ እሳተ ገሞራ በእንዶኔዝያ ፈነዳ፤ 3600 ሰዎች ሞቱ።
- 1892 - የእንግሊዝ ሃያላት በአፍሪካነር (ቦር) ጦርነት (ደቡብ አፍሪቃ) በበርገንዳል ውጊያ አሸነፉ።
- 1920 - ጦርነት የሚከላከል የኬሎግ-ብሪያንድ ውል በ60 አገሮች ተፈረመ።
ነሐሴ 22 ቀን: ነጻነት በዓል በሆንግኮንግ...
- 1601 - ጋሊሌኦ ስለመጀመርያ ቴሌስኮፕ ለቬኒስ አማካሪዎች መግለጫ ሰጠ።
- 1805 - ናፖሌዎን በድረስደን ውጊያ ድል አደረገ።
- 1888 - ከዓለሙ ታሪክ አጭሩ ጦርነት - 38 ደቂቃ - የእንግሊዝ-ዛንዚባር ጦርነት።
- 1955 - ዶ/ር ማርቲን ሉጠር ኪንግ «እኔ ሕልም አለኝ» ያለበትን ቃል ለሰላማዊ ሰልፍ ተናገረ።
- 1982 - ሳዳም ሁሰይን ኩወይት የኢራቅ ክፍላገር ነው ይላል።
- 1768 - የእንግሊዝ ሠራዊት በጆርጅ ዋሽንግተን ላይ በሎንግ አይላንድ ውጊያ አሸነፉ።
- 1822 - መጀመርያ የምድር ባቡር አገልግሎት "ዘ ቶም ሳምብ" በዩናይትድ ስቴትስ ጀመረ።
- 1871 - በደቡብ አፍሪቃ መጨረሻ የሆኑት የዙሉ ንጉሥ ከትሿዮ በእንግሊዞች ተማረከ።
- 1941 - የሶቭየት ኅብረት መጀመርያውን ንዩክሌያር መሣሪያ በፈተና አፈነዳ።
- 1987 - ናቶ በቦስኒያ ሰርቦች ላይ ዘመቻ ጀመረ።
ነሐሴ 24 ቀን: የድል ቀን በቱርክ (የ 1922 ዱምሉፒናር ድል ለማስታወስ)፤ የቅዱስ ሮዛ በዓል በፔሩ...
- 1934 - የአላም አል ሓልፋ ውጊያ በጀርመንና እንግሊዝ ታንኮች መኃል በግብፅ በረሃ ጀመረ።
- 1959 - ጡርጉድ ማርሻል መጀመርያ አፍሪቃ-አሜሪካዊ የዋና ብሔራዊ ችሎት ፈራጅ ተሾሙ።
ነሐሴ 25 ቀን: የነጻነት በዓል በማለይዝያ፤ ትሪኒዳድ፤ ኪርግዝስታን...
- 1557 - በዩናይትድ እስቴት ከሁሉ አስቀድሞ በአውሮጳውያን የተሰራ ከተማ ሰይንት ኦገስቲን ፍሎሪዳ ተመሰረተ።
- 1792 - ጌብሪየል ፕሮሰር የባርዮችን ብጥብጥ በሪችሞንድ ቪርጂንያ አሸፈተ።
- 1805 - ክሪክ የተባለው የቀይ ኢንዲያን ጐሣ ወታደሮች በፎርት ሚምስ ምሽግ አላባማ ላይ እልቂት አደረጉ።
- 1854 - በአሜሪካ መነጣጠል ጦርነት ደቡብ ክፍላገሮች (ኮንፌዴራቶች) በ2ኛ መናሠሥ ውጊያ አሸነፉ።
- 1984 - ፓስካል ሊሱባ በኮንጎ ሪፑብሊክ ምርጫ ፕሬዚዳን ሆኑ፤ ይህ ምርጫ የረጅም ዘመን አንድ ፓርቲ ግዛት ጨረሰ።
- 1990 - ስሜን ኮሪያ የራሱን ሰው ሠራሽ መንኮራኩር መጀመርያ ጊዜ ላከ።
ነሐሴ 26 ቀን: የሕገመንግስት ቀን በስሎቫኪያ...
- 1878 - ከምድር መንቀጥቀጥ በሳውስ ካሮላይና 100 ሰዎች ሞቱ።
- 1915 - ታላቅ ምድር መንቀጥቀጥ በጃፓን መቶ ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ገደለ።
- 1931 - አዶልፍ ሂትለር ፖሎኝን በመውረሩ ሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት ጀመረ።
- 1961 - መንፈቅለ መንግስት በሊቢያ ሙአማር ጋዳፊን ከፍ አደረገው።
- 1975 - የኮሪያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሶቭየት ኅብረት ላይ ሲተኮስ 269 መንገደኞች ሞቱ።
- 1983 - ዑዝበክስታን ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
ነሐሴ 27 ቀን: ብሔራዊ በዓል በቬትናም...
- 1865 - በአባታቸው በምፓንዴ መሞት ከትሿዮ የዙሉ ንጉስ ሆኑ።
ነሐሴ 28 ቀን: ነጻነት በዓል በቃጣር...
- 1862 - የፕሩሲያ (ጀርመን) ሠራዊት 3ኛ ናፖሊዎንን ከ100,000 ጭፍሮች ጋር በሰዳን ውግያ አሸነፈ።
- 1890 - በኦምዱርማን ውግያ ሱዳን የእንግሊዝ ሠራዊት ድል በማድረግ ቅኝ አገር አደረጉት።
- 1935 - በ2ኛ አለማዊ ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቹ ሃያላት ተወረረች።
- 1946 - የቻይና ሃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ።
ነሐሴ 29 ቀን: የአባቶች ቀን በአውስትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ...
- 1784 - በፈረንሳይ አብዮት ከ200 በላይ ቄሳውንት ሰማዕትነት አገኙ።
- 1830 - በሜሪላንድ ፍረድሪክ ዳግላስ መርከበኛ በማስመስል ከባርነት አመለጠ።
- 1949 - የአርካንሳው አገረ ገዥ ኦርቪል ፋውበስ ጥቁር ትማሮች ከነጭ ጋራ እንዳይማሩ የክፍላገሩን ወታደሮች በሊተል ሮክ ሰበሰበ።
ነሐሴ 30 ቀን: አስተማሮች ቀን በሕንደኬ (የራዳክሪሽናን ልደት)...
- 402 - ሮማ በቪዚጎቶች ተዘረፈች።
- 1641 - በኢጣልያ ካስትሮ የሚባል ከተማ በሮማ ፓፓ ላይ አመጽ አድርጎ፡ የፓፓ ሃያላት አጠፉት።
- 1658 - በለንደን እንግሊዝ 10 ሺህ ሕንጻዎች ያጠፋ ታላቅ እሳት ጀመረ።
- 1775 - የአሜሪካ ነጻነት አብዮት ከእንግሊዝ በፓሪስ ውል ተጨረሰ።
- 1790 - የአንድ ሳምንት ባሕር ውግያ በእንግሊዝና በእስፓንያ መካከል ከቤሊዝ አጠገብ ጀመረ።
- 1878 - ከ30 አመት ትግል በኋላ፣ የአፓቺ አለቃ ጀሮኒሞ በአሪዞና እጅን ሰጠ።
ጳጉሜ 1 ቀን: ነጻነት ቀን በስዋዚላንድ፣ አንድነት ቀን በቡልጋሪያ...
- 1773 - ሎስ አንጅለስ የምትባል ከተማ በ44 እስፓንያውያን ሠፈረኞች ተመሰረተች።
- 1828 - ሳሙኤል ሁስተን የቴክሳስ ሬፑብሊክ መጀመርያ ፕሬዚዳን ሆኖ ተመረጠ።
- 1869 - የላኮታ ኢንዲያን አለቃ ክሬዚ ሆርስ በእስር ተገደለ።
- 1893 - ሌኦን ቾልጎሽ የተባለ ወንበዴ የአሜሪካ ፕሬዚዳን መኪንሊ ተኩሶ ገደለው።
- 1907 - ታንክ የሚባል የጦርነት መሳርያ ለመጀመርያ ጊዜ በእንግሊዞች ተፈተነ።
- 1947 - በኢስታንቡል ቱርክ በኖረበት በግሪክ ህብረተሰብ ላይ እልቂት ተደረገ።
ጳጉሜ 2 ቀን: ነጻነት ቀን በብራዚል፣ የድል ቀን በሞዛምቢክ...
- 1785 - የፈረንሳይ አብዮታዊ አማካሪዎች "የማስፈራራት መንግስት" ዐዋጁ።
- 1932 - ጀርመኖች በ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት ለንደንን በቦምብ ለመደብደብ ጀመሩ።
- 1969 - የአሜሪካ ፕሬዚዳን ጂሚ ካርተር የፓናማ ካናል አስተዳደር ለፓናማ በ1992 ለማዛወር ውል ፈረሙ።
- 1978 - ዴስሞንድ ቱቱ በኤጲስቆፖሳዊ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ መጀመርያ ጥቁር ኤጲስ ቆጶስ ሆኑ።
- 1988 - የራፕ ሙዚቃ ተጫዋች ቱፓክ ሻኩር በላስ ቬጋስ ተተኲሶ ተገደለ።
- 71 - ደብረ ቬሱቪዩስ እሳተ ገሞራ በኢጣልያ 3 ከተሞችን አጠፋ።
- 1690 - ፃር 1 ፕዮትር በሩሲያ የጺም ቀረጥ አስገበረ።
- 1804 - ናፖሊዎን በሩሲያ ላይ በቦሮዲኖ ውግያ ድል አደረገ።
- 1814 - ብራዚል ነጻነቱን ከፖርቱጋል አዋጀ።
- 1892 - አንድ ታላቅ አውሎ ንፋስ በቴክሳስ 8000 ሰዎች አጠፋ።
- 1935 - የአሜሪካ ጄኔራል አይዘንሃወር የኢጣልያ እጅ መስጠት በጦርነት አዋጀ።
ጳጉሜ 4 ቀን: ሬፑብሊክ ቀን በስሜን ኮርያ፣ ነጻነት ቀን በታጂኪስታን፣ ብሄራዊ ቀን በቡልጋርያ...
- 467 - የጀርመን አለቃ ኦረስቴስ የሮማ ነጉስን አባርሮ መጨረሻውን ንጉስ ሮሙሉስ አውጉስቶስን ሾመ።
- 1514 - ቪክቶሪያ የምትባል መርከብ ወደ ስፓንያ በመመለሷ መጀመርያ ዓለምን የከበበችው መርከብ ሆነች።
- 1914 - ቱርኮች በግሪክ-ቱርክ ጦርነት አሸንፈው ስሚርና ከተማ ተቃጠለ።
- 1963 - በአቲካ እስር ቤት ኒው ዮርክ ሁከት ተደረገ።
ጳጉሜ 5 ቀን: ብሄራዊ ቀን በጂብራልታር...
- 1252 - እጣልያ የንጉስ ወገን በፓፓ ወገን በሞንታፔርቲ ድል አደረገ።
- 1831 - ጆን ኸርሸል መጀመርያ ፎቶ አነሳ።
- 1911 - በሳንዠርመን ውል ዩጎስላቪያ፣ ሃንጋሪና ቸኮስሎቫኪያ ከኦስትሪያ ነጻነታቸውን አገኙ።
- 1934 - በ2ኛ አለማዊ ጦርነት የጓደኞች ሃያላት በማጁንጋ ማዳጋስካር ደረሱ።
- 1966 - ጊኔ-ቢሳው ነጻነቱን ከፖርቱጋል አገኘ።
- 1994 - ገለልተኛ አገር የሆነ ስዊስ በመጨረሻ የተባበሩት መንግስታት አባል ሆነ።
ጳጉሜ 6 ቀን
- 1731 - በቻርልስተን ሳውስ ካሮላይና አካባቢ ስቶኖ የባርዮች አመጽ ሆነ።
- 1979 - የሬጌ ሙዚቃ ዘፋኝ ፒተር ቶሽ ቤቱ በኪንግስተን ጃማይካ በሌቦች ተገደለ።