ላሊበላ
ከWikipedia
ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ12.04° ሰ 39.04° ምዕ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባህር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትሆን የህዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በሁለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመሆን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው።
የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እንደተሰሩ የሚታመን ሲሆን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ፀሃፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ነጉስ ላሊበላ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው የባላል። የምናየውን ቤተክርስቲያን የሰራው ንጉስ ላሊበላ ነው ይባላል። ላሊበላ ቤተክርስቲያኑን ዎደታች ነው የሰራው፣ ሌሎቾ ውድ ላይ ሲሆኑ። ንጉስ ላሊበላ ቤተክርስቲያኑን የስራው በመላእክት ተነግሮት ነው ይባላል።
ኢትዮጵያ |
ታሪካዊ ቦታዎች - አክሱም | ላሊበላ | ጎንደር | ነጋሽ | ሐረር | ደብረ-ዳሞ | አዲስ አበባ |