ሶማሌ ክልል
ከWikipedia
የሶማሌ ክልል (ክልል 5) ከኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። ዋና ከተማው ጅጅጋ ነው። 279,252 ካሬ ኪ.ሜ. ቦታ ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 3,602,000 ነበር። ክልሉ በጣም ብዙ የሶማሌ ብሔረሰቦች ይገኙበታል። በ1970ዎቹ እ.ኤ.አ. ሶማሊያ ቦታውን በወውረር ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አስነስታ ነበር። ከነዚህም ዋነኛው የኦጋዴን ጦርነት ነው።
በአፕሪል 2005 እ.ኤ.አ. ከባድ ዝናብ በክልሉ እና ሶማሊያ ጎርፍ አስከትሏል። ይህም የሸበሌ ወንዝን አንዲሞላና አካባቢውን በውሃ እንዲያጥለቀልቅ አድርጓል። ይህ ደግሞ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሞት አስከትሏል።
ኢትዮጵያ |
ታሪካዊ ቦታዎች - አክሱም | ላሊበላ | ጎንደር | ነጋሽ | ሐረር | ደብረ-ዳሞ | አዲስ አበባ |