ጥንታዊ እንግሊዝኛ
From Wikipedia
ጥንታዊ እንግሊዝኛ (Englisc /ኧንግሊሽ/) በእንግሊዝ አገር ከ440 ዓ.ም. ገደማ እስከ 1100 ዓ.ም. ያሕል የተናገረ ቋንቋ ነበር. ዛሬ ጀርመንና ዴንማርክ ከተባሉት አገሮች ፈልሰው በእንግሊዝ በተስፈሩት ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ቀድሞ አይነት ነው. ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል. ቅርብ ዘመዶቹ ጥንታዊ ፍሪዝኛ እና ጥንታዊ ሴክስኛ ናቸው.
ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት. በተለይ በስሜን እንግሊዝ የኖሩት የአንገሎች መነጋገርያ በደቡብ ከኖሩት ከሴክሶች ትንሽ ተለያየ.
ከ800 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ስሜኑ በቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ. ቢሆንም የቫይኪንጎች ቋንቋ ኖርስኛ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ጋር ዝምድና ነበረውና ከኖርስኛ አያሌው ቃላት ወደ እንግሊዝኛ ገቡ. ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቃላት sky /ስካይ/ (ሰማይ) leg /ለግ/ (እግር) እና they /ዘይ/ (እነሱ) የደረሱ ከኖርስኛ ነበር.
የተማሩ ሰዎች (መምህራን ወይም ቄሶች) በብዛት የሮማይስጥ ዕውቀት ስለነበራቸው ደግሞ ከሮማይስጥ ተጽእኖ አንዳንድ ቃላት የዛኔ ወደ እንግሊዝኛ ተበደሩ. ንጉሥ አልፍሬድ እራሳቸው ብዙ መጻሕፍት ከሮማይስጥ አስተረጎሙ.
ኖርማኖች እንግሊዝን በ1059 ከወረሩ ጀምሮ ቋንቋው ከትምህርት ቤት ስለ ተከለከለ በየጥቂቱ ባሕርዩ እጅግ ተለወጠ.
በጥንታዊ እንግሊዝኛ እያንዳንዱ ስም የተወሰነ ጾታ (ወንድና ሴት) ነበረው. ለምሳሌ sēo sunne /ሴዮ ሱነ/ (ፀሐይቱ) አንስታይ, se mōna /ሴ ሞና/ (ጨረቃው) ተባዕታይ ነበር.
ይዞታ |
[ለማስተካከል] ጽሕፈት
ቋንቋው መጀመርያ ፉሶርክ በተባለው የሩን ፊደል ሲጻፍ ክርስትና ከተቀበለ በኋላ ግን በላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ. አንዳንድ ተጨማሪ ፈደላት እንዲህ ነበሩ:
- ȝ - ይህ ፊደል (ከአይርላንድኛ ተበድሮ) እንደ 'ይ' ወይም 'ግ' ወይም 'ኅ' ሊጠቀም ይችል ነበር.
- ð - ይህ ፊደል ከላቲን d ተቀይሮ እንደ 'ስ' ወይም 'ዝ' ሊጠቀም ይችል ነበር.
- þ - ይህ ከቀድሞው ፉሶርክ ተበድሮ ደግሞ እንደ ስ ወይም ዝ ጠቀመ.
- ƿ - 'W' የሚለው ፊደል ገና ስላልኖረ 'ው' ለመጻፍ በዚህ ፊደል (ከፉሶርክ ተበድሮ) ነበር. በኋላ ዘመን ከp (ፕ) ጋር ስላለው ተመሳሳይነት ይህ ፊደል ጠፋ. ስለዚህ የዛሬ ሊቃውንት ጥንታዊ እንግሊዝኛ የሚጽፉ በዘመናዊው 'w' ነው.
[ለማስተካከል] ምሳሌ
[ለማስተካከል] የጌታ ጸሎት (አባታችን ሆይ)
- Fæder ure þu þe eart on heofonum,
- Si þin nama gehalgod.
- To becume þin rice,
- gewurþe ðin willa, on eorðan swa swa on heofonum.
- urne gedæghwamlican hlaf syle us todæg,
- and forgyf us ure gyltas, swa swa we forgyfað urum gyltendum.
- and ne gelæd þu us on costnunge, ac alys us of yfele. soþlice.
- ፋደር፡ ኡረ፡ ዙ፡ ዘ፡ ኤየርት፡ ኦን፡ ሄዮቮነም,
- ሲ፡ ዚን፡ ናማ፡ ይሃልጎድ.
- ቶ፡ በኩመ፡ ዚን፡ ሪቸ,
- ይዉርሰ፡ ዚን፡ ውላ, ኦን፡ ኤዮርሳን፡ ሷ፡ ሷ፡ ኦን፡ ሄዮቮነም.
- ኡርነ፡ ይደይኋምሊቻን፡ ህላፍ፡ ሲውለ፡ ኡስ፡ ቶደይ,
- አንድ፡ ፎርዪውፍ፡ ኡስ፡ ኡረ፡ ዪውልታስ, ሷ፡ ሷ፡ ዌ፡ ፎርዪውቫስ፡ ኡረም፡ ዪውተንደም.
- አንድ፡ ነ፡ ይለይድ፡ ዙ፡ ኡስ፡ ኦን፡ ኮስትኑንገ, አክ፡ አሊውስ፡ ኡስ፡ ኦፍ፡ ኢውቨለ. ሶስሊቸ.
[ለማስተካከል] የውጭ መያያዣዎች
- The Electronic Introduction to Old English
- First steps in Old English - a course for absolute beginners
- Old English (Anglo-Saxon) alphabet
- Bosworth and Toller, An Anglo-Saxon dictionary
- Old English - Modern English dictionary
- The Origins of Old English
- Shakespeare's English vs Old English
- Guide to using Old English computer characters (Unicode, HTML entities, etc.)
- Dictionary of Old English Project at the University of Toronto
- The Germanic Lexicon Project
- Text Collections - Texts and Translations