ማልትኛ
From Wikipedia
ማልትኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። በሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ በሚገኘው ደሴት አገር በማልታ ላይ ይናገራል። መንስኤው ከቅርብ ዘመዱ ከአረብኛ ነው። ከሁሉ የሚመስለው የቱኒዚያ አረብኛ ሆኖም ከማልታ ቅርብ ጊዜ ታሪክ የተነሣ ብዙ ቃላትና ድምጽ ከጣልኛ እና ከእንግሊዝኛ ወስዷል።
ከሴማውያን ቋንቋዎች ሁሉ ማልትኛ ብቻ በላቲን አልፋቤት የተጻፈ ነው። በ1928 ዓ.ም. ማልትኛና እንግሊዝኛ የደሴቱ መደበኛ ቋንቋዎች ተደረጉ። ከዚያ ዓመት በፊት መደበኛው ቋንቋ ጣልኛ ነበር። ዛሬ የተናጋሪዎቹ ቁጥር 371,900 ነው። ከነዚህም ውስጥ በአውስትራሊያ፥ አሜሪካና ካናዳ የሚችሉት ይገኛሉ።
በማልትኛ ከሁሉ መጀመርያው ሰነድ በ1460 ዓ.ም. አካባቢ በፔትሮ ካሻሮ የተቃኘው ግጥም ካንቲሌና ነው። ይሁንና ለረጅም ዘመን ማልትኛው ስነ-ጽሑፋዊ ሳይሆን በብዛት የመነጋገርያ ቋንቋ ነበርና ጽሕፈት የተደረገው በአረብኛ በኋላም በጣልኛ ነበር።
ይዞታ |
[ለማስተካከል] ስዋሰው
የማልትኛ ስዋሰው መሠረት ከአረብኛ ሲሆን ከሮማንስ ቋንቋዎች በተለይ ከሲሲልኛና ከኖርማንኛ ቀበሌኞች ጽኑእ ተጽእኖ ይገኛል።
ቅጽል በስም ይቀደማል። እንደ አረብኛ ወይም እንደ ዕብራይስጥ መስተፃምሩ በስምና በቅጽል ይታያል። ለምሳሌ It-tifel il-kbir ኢት-ቲፈል ኢል-ክቢር = ትልቁ ልጅ። ይህ ደንብ ግን ከሮማንስ ቋንቋዎች ለተበደሩ ስሞች ወይም ቅጽሎች አይደለም።
የስም ቁጥር የሚታይበት ዘዴ ለሮማንስና ለሴማዊ ቃላት ይለያያል። እንደተለመደ ለሴማዊ ስሞች ብዙ ቁጥር ለማመልከት -iet ወይም -ijiet (-የት, -ኢየት) ይጨመር። ለምሳሌ art፥ አርት (መሬት) => artijiet፥ አርቲየት (መሬቶች) ይሆናል። ደግሞ እንደ ሴማውያን ልሣናት ለአንዳንድ ስሞች 'ሰባራ ብዙ ቁጥር' ይገኛል፣ ለምሳሌ ktieb ክትየብ (መጽሐፍ) => kotba ኮትባ (መጻሕፍት)፣ raġel ራጀል (ሰው) => irġiel ኢርጅየል (ሰዎች)።
ለሮማንስ ስሞች ግን የብዙ ቁጥር ባዕድ መነሻ -ኢ (-i) ሊሆን ይችላል. ለምሳሌ lingwa፥ ሊንጓ (ቋንቋ) => lingwi, ሊንግዊ (ቋንቋዎች)።
ግሦች እንደ ሌሎች ሴማውያን ቋንቋዎች ይመስላሉ። ከተናባቢዎች ሥር ይሠራሉ ማለት ነው። ለምሳሌ 'እኛ ጻፍን' በማልትኛ ktibna 'ክቲብና'፥ በአረብኛ 'ካታብና'፥ በዕብራይስጥም ካታቭኑ ይባላል። ከሮማንስ ለተበደሩ ግሦች ቢሆንም የአረብኛ ባዕድ መነሻ ይጨመራል፥ ለምሳሌ iddeċidejna (ኢደቺደይና) 'እኛ ወሰንን'።
[ለማስተካከል] ምሳሌ (ከተመድ መብቶች ጽሑፍ)
ማልትኛ:
- Il-bnedmin kollha jitwieldu ħielsa u indaqs fid-dinjità u l-jeddijiet. Huma mogħnija bir-raġuni u bil-kuxjenza u għandhom iġibu ruħhom ma' xulxin bħala aħwa.
አጠራር:
- ኢል-ብነድሚን ኮላ ዪትውየልዱ ሕየልሳ ኡ ኢንዳእስ ፊት-ዲንዪታ ኡ ል-የዲየት። ኡማ ሞዕኒያ ቢር-ራጁኒ ኡ ቢል-ኩሽየንጻ ኡ ዓንዶም ኢጂቡ ሩሖም ማ ሹልሺን ብሓላ አሗ።
አማርኛ:
- የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ የማስተዋልና ኅሊናው ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።
[ለማስተካከል] ፊደል
የማልትኛ ፊደል ከላቲን አልፋቤት መጥቶ እንዲህ ነው።
A B Ċ D E F Ġ G Għ H Ħ I Ie J K L M N O P Q R S T U V W X Ż Z
a b ċ d e f ġ g għ h ħ i ie j k l m n o p q r s t u v w x ż z
(Y, y) የሚለው ላቲን ፊደል በማልትኛ የለም።
ፊደል | ድምጽ በአማርኛ | ስለ አጠርር |
---|---|---|
A | አ | እንደ ተለመደው |
B | ብ | እንደ ተለመደው፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ፕ' ይሰማል። |
Ċ | ች | ለዚህ ቋንቋ Ċ ልዩ ፊደል ነው |
D | ድ | እንደ ተለመደው፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ት' ይሰማል። |
E | ኧ | |
F | ፍ | እንደ ተለመደው |
Ġ | ጅ | ለዚህ ቋንቋ Ġ ልዩ ፊደል ነው፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ች' ይሰማል። |
G | ግ | እንደ ተለመደው፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ክ' ይሰማል። |
GĦ | ዕ | ልዩ ፊደል ነው፤ የአናባቢውን ጸባይ እንደ አረብኛ ع ይለውጣል |
H | አይሰማም፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ሕ' ይሰማል | |
Ħ | ሕ | ልዩ ፊደል ነው፤ እንደ አረብኛ ح ይሰማል |
I | ኢ | እንደ ተለመደው |
IE | የ, ኢ | |
J | ይ | |
K | ክ | እንደ ተለመደው |
L | ል | እንደ ተለመደው |
M | ም | እንደ ተለመደው |
N | ን | እንደ ተለመደው |
O | ኦ | |
P | ፕ | እንደ ተለመደው |
Q | እ | ተፈናጣሪ ድምጽ እንደ አረብኛ ﺍ |
R | ር | እንደ ተለመደው |
S | ስ | እንደ ተለመደው |
T | ት | እንደ ተለመደው |
U | ኡ | እንደ ተለመደው |
V | ቭ | እንደ ተለመደው፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ፍ' ይሰማል። |
W | ው | እንደ ተለመደው |
X | ሽ / ዥ | |
Ż | ዝ | ልዩ ፊደል ነው፤ በቃል መጨረሻ ግን እንደ 'ስ' ይሰማል። |
Z | ጽ |