የሜዳ አህያ
From Wikipedia
የሜዳ አህያ በላቲን Equidae የሚባለው ፈረስ በተሰብ አባል ሲሆን ፣ ከመካከለኛው እስከ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ይገኛል። ነጭና ጥቁር ሰንጠረዥ የለበሰው ቆዳቸው አንድ ምልክታቸው ነው።
የዱር አራዊት የሚያጠኑ ባለሞያዎች (zoologist) የሜዳ አህያ ነጭና ጥቁር ባለሰንጠረዥ ቆዳ ከሚያድኑት አራዊት ለመሰወር እንደሚጠቅመው ይናገራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ አንድ የሜዳ አህያ ከረዣዥም ሣሮች መሃል ሲሆን አብሶ አንበሳ ለይቶ ለማየት እንደሚከበደው በመጠቆም ነው። ለዚህም ዋነኛው ምክኒያት አንበሳ ቀለም ስለማይለይ ነው።