Web Analytics


https://www.amazon.it/dp/B0CT9YL557

We support WINRAR [What is this] - [Download .exe file(s) for Windows]

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
SITEMAP
Audiobooks by Valerio Di Stefano: Single Download - Complete Download [TAR] [WIM] [ZIP] [RAR] - Alphabetical Download  [TAR] [WIM] [ZIP] [RAR] - Download Instructions

Make a donation: IBAN: IT36M0708677020000000008016 - BIC/SWIFT:  ICRAITRRU60 - VALERIO DI STEFANO or
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ኤድስ

ኤድስ

ከWikipedia

ኤድስ በአፍሪቃ
ኤድስ በአፍሪቃ

ኤድስ ወይም Acquired Immune Deficiency Syndrome (AIDS) በመባል የታወቀው በሽታ የሚመጣው ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ Human Immunodeficiency Virus (ኤችአይቪ HIV) በሚባል ጀርም ነው። በሽታው የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ ነጭ ሴሎችን በማጥፋት ለቀላል በሽታዎች ለሕይወት ኣስጊ የመሆን ዕድል በመስጠት የሚገድል ነው። የሚተላለፈው ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ያልፀዳ መርፌ በመጠቀም ወይም ኣስፈላጊዎቹ ጥንቃቄዎች ሳይደረጉ በሚፈጸሙ የተለያዩ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች ነው። ኤድስን የሚያመጣው ሕይወት ያለው ጥገኛ ጠንቅ በኃይለኛ የማጉሊያ መሣሪያዎች ይታያል። ቫይረሱ ሰውነት ውስጥ እያለ እስከ ፰ ዓመታት የማይታመሙና በሽታውን የሚያስተላልፉ ጤነኛ ሰዎች ኣሉ።
የኤድስ በሽታ ሲጀምር ሰውነት ወይም ኣካላችን በቀላሉ የሚከላከላቸው ጀርሞች እንደፈለጋቸው በመባዛት ለሕይወት ኣደገኛ ሆነው ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ጤነኛ መድን በነበረን ጊዜ ከማይተናኮሉን ባክቴሪያዎች ኣንዱ ኒሞንያ ያስከትላል። የቆዳ ካንሰር (Kaposi's Sarcoma) እና የኣንጎል በሽታም ሊኖሩ ይችላሉ። AIDS-related complex (ARC) ወይም ኣርክ የሚባሉ ምልክቶችም ሊመጡ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል የንፍፊት ማበጥ፣ የማይለቁ ትኩሳቶች፣ ድካምና ተቅማጥ፣ ክብደት መቀንስ (ከ፲ በ፻ በላይ)፣ ደረቅ ሳልና ከባድ የእንቅልፍ ላብ ይገኙበታል። ትረሽ (Thrush) እና ሽንግልስ (Shingles) የሚባሉ በሽታዎችም ሊኖሩ ይችላሉ።

ኤድስ እንዳይዝ የምንከላከልበት የክትባት ዘዴ የለም። በሽታው ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። በኣሁኑ ጊዜ ያለን መከላከያ በበሽታው እንዳንያዝ ኣስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎች ማድረግ ብቻ ነው። በሽታው እንዴት እንደሚተላለፍ በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን በመከታተል ተረድቶ ቫይረሶቹ እንዳይሰራጩ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን ይገባል። ኤድስ ኣሰቃቂና ኣደገኛ በሽታ ቢሆንም እንደጉንፋን በቀላሉ የሚተላለፍ ስላልሆነ ልንከላከለው የምንችለው በሽታ ነው። ስለ በሽታው በሰፊው ማወቅ ባንፈልግ እንኳን በበሽታው እንዳንያዝ እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት እንደምንጠነቀቅ ማወቅ እንደሚጠቅሙ ተረጋግጧል።

ኤድስ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1970 ዓ.ም. ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 እ.ኤ.አ. ድረስ የተበከለ ደም በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ያለቅብጠታቸው በበሽታው ተይዘዋል። ከ1988 ወዲህ ግን ኤድስ ሲይዝ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody) በመመርመር የኤድስ ቫይረስ እንዳጋጠመን የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በተለይ የደም ማነስን ለመከላከል ሆስፒታል ከሚሰጠን ደም በመተላለፍ ሊይዝ የሚችለው ኤድስ ወደ መጣፋቱ ደርሷል።

ይዞታ

[ለማስተካከል] መተላለፍ

ኤድስ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላል።

ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን የድረግ (Drugs) መርፌ ሌላ ሰው ቢጠቀምበት (Intravenous) በቫይረሱ መተላለፍ የተነሳ በበሽታው መያዝ ይቻል ይሆናል።

በበሽታው ከተያዘ ወይም ቫይረሱ ካለበት ማንኛውም ሰው (ወንድ ወይም ሴት) ጋር የግብረ ሰዶም ግንኙነት (Homosexual, bisexual intercourse) በማድረግ በሽታው ሊይዝ ይችላል።

ኤድስ ቫይረሱ ወይም በሽታው ካለበት ሰው ጋር በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (Heterosexual intercourse) የሚይዝ የኣባለ ዘር በሽታ ሆኗል።

ቫይረሱ ያለባት እናት በሽታውን (ማህፀን ውስጥና በምትወልድበት ጊዜም) ለሕፃንዋ ማስተላለፍ (Intrauterine, perinatal) ትችላለች።

በበሽታው የተያዘች እመጫትን የጡት ወተት በመጥባት (በመጠጣት) ሕፃናትን በሽታው ሊይዛቸው (Oral) ይችላል።

[ለማስተካከል] መከላከያ

ከኤድስ በሽታ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል።

ከማንኛውም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት (ከተቻለ) መቆጠብ፣ ወይም ቫይረሱ ካሌለበት ኣንድ ታማኝ የፍቅር ጓደኛ ሌላ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኣለማድረግ።

ለረዥም ጊዜ ተማምነው ኣብረው የቆዩ ባልና ሚስት መስጋትና ለኤድስ ሲባል በኮንዶም (Condom) መጠቀም የለባቸውም። ታማኝነት ከመቼውም ጊዜ ኣሁን ኣስፈላጊ ነው።

የሚወጉ ድራጎች (እተደበቁ ተሰባስበው ባልፀዱ መሣሪያዎች ከሚወስዱ ጋር) ኣለመውሰድ። በሽታው ከያዘው ሰው ጋር መርፌና ሲሪንጋ ኣለመጋራት።

ከማያውቁት ሰው ወይም ከብዙ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግ ከቆዩ (ኣመንዝራ) ጋር ማንኛውንም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኣለማድረግ።

ቫይረሱ እንዳሌለበት ከማያውቁት (ወይም በሽታው ከያዘው) ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ካስፈለገ የሚከተሉትን ፬ ጥንቃቄዎች መከተል ያስፈልጋል።

የኤድስ ቫይረስ ያለባቸው የተለያዩ የኣባለ ዘር ፍሳሾች (Semen, vaginal secretions) ወደ ሌላ ሰው (ብልት፣ ኣፍ፣ ፊንጢጣ ወዘተ...) እንዳይገቡ መጠንቀቅ።

የኤድስ መኖር ካጠራጠረ የግብረ ሥጋው ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት ወንድየው የላቴክስ (Latex) ላስቲክ ኮንዶም ብልቱ ላይ ማድረግ ኣለበት። ከቆዳ የሚሠራው ዓይነት ኮንዶም ለኤድስ መከላከያ ኣይሠራም።

ለተጨማሪ ጥንቃቄ እስፐርሚሳይድስ (Spermicide) ቫይረሶቹን የመግደል ጥቅም ስላላቸው የኮንዶሙን ውጭና ጫፍ ማነካካት ሳይጠቅም ኣይቀርም።

ከደረቁ ይልቅ ቅባት (Lubricant) ያለው የላቴክስ ኮንዶም እንዳይቀደድም ይመረጣል። በውሃ (Water-base) በተበጠበጠ እንጂ እንደ ቫስሊን የኣሉ ነዳጅ ዘይት (Oil-based) የሚበጠበጡ ቅባቶች ኮንዶሙን ስለሚበሳሱ ኣለመጠቀም ጥሩ ነው። ፓኬቱ ላይ የተጻፈውን ማንበብ ያስፈልጋል። ከፈቃደ ሥጋው ግንኙነት በኋላ ላቴክሱን በጥንቃቄ ማውጣት መረሳት የለበትም።

[ለማስተካከል] ተጨማሪ መረጃ

በተጨማሪም የሚከተሉት ታውቀዋል።

የኣንድ ሰው ደም ወደ ሌላው (በብዛት) ሊተላለፍባቸው የሚችልባቸውን ቍሳቁስ ለሌላ ከማዋስ መቆጠብ። ለምሳሌ ያህል የጺም መላጭያ፣ ጥርስ ብሩሽና መፋቂያ የመሳሰሉትን ኣለመዋዋስ። ደም መበካከልን ሊያስከትሉ የሚችሉ ባህሎች ከኣሉ ማረም ወይም እንዲጠፉ ማበረታታት።

የኤድስ ቫይረስ ሊኖርባቸው የሚችሉ ደምና የመሳሰሉትን ጓንት (እና እንዳስላጊነቱም ማስክ) ሳያደርጉ ኣለመነካካት።

ስለበሽታው ለማያውቁ ማሰማትና ለልጆች ማስተማር እንዲሁም ኤድስ ያለባቸውን በሚቻለን ሁሉ የመርዳት ኃላፊነትና በየጊዜው የሚገኙትን የምርምር ውጤቶች ለማወቅ መሞከርና ይኸንኑ ዕውቀት ማሰራጨት ኣለብን።

የኤድስ ቫይረስ ደካማ በመሆኑ ከኣካል ውጭ ለረዥም ጊዜ ኣይኖርም። (እንደ ዕቃው ዓይነት የተነካኩትን ለዓሥር ደቂቃዎች ማፍላት ወይም ኣንድ በመቶ ብሊች ባለው ውሃ መዘፍዘፍ ቫይረሶቹን ሊገድል ይችል ይሆናል።

ኣንድን ሰው የበሽታው ቫይረስ እንዳላጋጠመው በተለያዩ (ተደጋጋሚ) የደም ምርመራዎች ማጣራት ይቻላል። (ኣስቀድሞም የኣካባቢውን የኤድስ ሕግ ማወቅ ጠቃሚ ነው።)

ኤድስ በመጨባበጥና በመሳሳም እንዲሁም በሽንትና በሰገራ፣ በወባ ትንኝና ቁንጫን በመሳሰሉት ደም መጣጮች ኣይላለፍም ተብሏል።

የኤድስ ቫይረስ (እራሱን ስለሚቀያይር ጥሩ ዓይነት) የመከላከያ ክትባት በቅርቡ ላይሠራ እንሚችል ተተምኗል። የቫይረስ በሽታዎችንም ማዳን በጣም ከባድ ስለሆነ (የኤድስም ቫይረስ ከሰው ጂን ጋር ስለሚካለስ) ፈዋሽ መድኃኒት በቅርቡ መገኘቱ ያጠራጥራል ይባላል። እስከዚያው ድረስ ግን በሽታው በየኣገሩ (ኢትዮጵያ ጭምር) መስፋፋቱን ስለቀጠለ ለሞት ከመማቀቅ ኣስቀድሞ ማወቅ የሚሻል ይመስለኛል። ቫይረሱ (ለረዥም ጊዜ) ከነበረባቸው መካከል ፺፱ በ፻ በበሽታው ተይዘዋል።

AZT (ኤዚቲ) እና የመሳሰሉት መድኃኒቶች ቫይረሱ እንዳይባዛ በመከላከል በሽታው እንዳይገድል ጊዜ ለመግዛት ይጠቅማሉ ይባላል።

የኤድስ መኖር ካጠራጠረ በጥሩ ጤንነት ለመኖር መሞከርና መድንን ከሚያዳክሙ መቆጠብ እንደሚራዱ ተገምቷል።

በሽታው በመካከላችን ስላለ ባለማወቅና በጥንቃቄ ጉድለት በኤድስ ብንያዝ ጥፋቱና ፀፀቱ የራሳችን ይመስለኛል። እስከ (1991) በዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የኤድስ ቫይረስ ከተገኘባቸው ፪፻፸ሺህ ሰዎች መካከል ፩፻ሺህ (፩00, 000) በበሽታው ሞተዋል። በዓለም ላይም (፩፶፬ ኣገሮች) ኣንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤድስ በሽታ ተይዘዋል። (ሕዝቡም መጠንቀቅ ካልጀመረ በቫይረሱ የሚበከለው ሰው ቍጥር በየዓመቱ እጥፍ እየሆነ ሊቀጥል እንደሚችልና ለማስታመምም ብዙ ብሊዮን ዶላርስ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል።) ግብረ ሰዶም የሚያዘወትሩና ድረግ የሚወጉ ሰዎች በሽታ ነው እየተባለ ቸል ሲባል ቆይቶ ኣሁን የሁላችንም ጠር መሆኑ ስለተደሰረበት የሚፈለግብንን ብናከናውንና (ከመንግሥታትም ጋር) ብንተባበር በሽታውን መቆጣጠር ይቻል ይሆናል። የፈንጣጣን በሽታ ከዓለም ለማጥፋት ከጠቀሙን መካከል ክትባትና የሕዝቡ ትብብር ዋናዎቹ ናቸው። ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማውራት ለማንኛውም ሕብረተሰብ ኣሳፋሪ ቢሆንም ኤድስ ያመጣብን ዱብ-ዕዳ የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ መወያየት መጀመር ኣለብን።

ይህ ጽሑፍ የተጻፈው የሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት ኣይደለም። በበለጠ ለመረዳት ሓኪሞቻችሁን ኣማክሩ። በ1988 እ.ኤ.አ. ለእያንዳንዱ የዩናይትድ እስቴትስ ቤተሰብ Understanding AIDS የተባለ ፰ ገጽ ጽሑፍ ከU.S. Department of Health and Human Services ሲላክ ወደ አማርኛ በነፃ በዶ/ር ኣበራ ሞላ ተተርጕሞና ተሰራጭቶ ነበር። የእዚህ የ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጽሑፍ መነሻ ይኸው የHHS Publication No. (CDC) HHS 88-8404 ጽሑፍ ነው።

[ለማስተካከል] የውጭ መያያዣዎች

Static Wikipedia 2008 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2007 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2006 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Sub-domains

CDRoms - Magnatune - Librivox - Liber Liber - Encyclopaedia Britannica - Project Gutenberg - Wikipedia 2008 - Wikipedia 2007 - Wikipedia 2006 -

Other Domains

https://www.classicistranieri.it - https://www.ebooksgratis.com - https://www.gutenbergaustralia.com - https://www.englishwikipedia.com - https://www.wikipediazim.com - https://www.wikisourcezim.com - https://www.projectgutenberg.net - https://www.projectgutenberg.es - https://www.radioascolto.com - https://www.debitoformtivo.it - https://www.wikipediaforschools.org - https://www.projectgutenbergzim.com