አንጎላ
ከWikipedia
|
|||||
ዋና ከተማ | ሏንዳ |
||||
ብሔራዊ ቋንቋ(ዎች) | ፖርቱጊዝ | ||||
መሪዎች ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ፈርናንዶ ዳ ፓይዳድ ዶስ ሳንቶስ |
||||
የነጻነት ቀን | ኅዳር 1 ቀን 1968 (Nov. 11, 1975 እ.ኤ.ኣ.) |
||||
የመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.) |
1,246,700 (ከዓለም 22ኛ) | ||||
የሕዝብ ብዛት (በ2004) |
10,978,552 (ከዓለም 71ኛ) | ||||
የገንዘብ ስም | ክዋንዛ | ||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | ||||
የስልክ መግቢያ | +244 |
አንጎላ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች ከንቲባዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቹጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።
[ለማስተካከል] የአመራር ክፍልፍል
ክልል | የሕዝብ ብዛት | የመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.) | ዋና ከተማ | |
1. | ቤንጎ | 450,000 | 33,016 | ካክሲቶ |
2. | ቤንጉዌላ | 600,000 | 1,788 | ቤንጉዌላ |
3. | ባኤ | 800,000 | 70,314 | ኩዊቶ |
4. | ካቢንዳ | 300,000 | 7,283 | |
5. | ኩዋንዶ ኩባንጎ | 140,000 | 199,049 | ሜኖንጉዌ |
6. | ኩዋንዛ ኖርቴ | 400,000 | 24,110 | ንዳላንታንዶ |
7. | ኩዋንዛ ሱል | 600,000 | 55,660 | ሱምቤ |
8. | ኩኔን | 200,000 | 87,342 | ኦንዲጂቫ |
9. | ሁዋምቦ | 1,000,000 | 34,270 | ሁዋምቦ |
10. | ሁኺላ | 700,000 | 75,002 | ሉባንጎ |
11. | ሉዋንዳ | 3,000,000 | 2,257 | ሉዋንዳ |
12. | ሉንዳ ኖርቴ | 103,000 | 103,000 | ሉካፓ |
13. | ሉንዳ ሱል | 125,000 | 77,637 | ሳውሪሞ |
14. | ማላንጄ | 850,000 | 97,602 | ማላንጄ |
15. | ሞክሲኮ | 230,000 | 223,023 | ሉኼና |
16. | ናሚቤ | 60,000 | 58,137 | ናሚቤ |
17. | ዩጂ | 800,000 | 58,698 | ዩጂ |
18. | ዛየር | 600,000 | 40,130 | ምባንዛ ኮንጎ |
በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች |
ሊቢያ| ላይቤሪያ| ሌሶቶ| የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ| ማሊ| ማላዊ| ማዳጋስካር| ሞሪሸስ| ሞሪታኒያ| ሞሮኮ| ምዕራባዊ ሣህራ| ሞዛምቢክ| ሩዋንዳ| ሱዳን| ሲሸልስ| ሳን ቶሜና ፕሪንሲፔ| ሴየራ ሌዎን| ሴኔጋል| ስዋዚላንድ| ሶማሊላንድ| ሶማሊያ| ቡሩንዲ| ቡርኪና ፋሶ| ቤኒን| ቦትስዋና| ቱኒዚያ| ታንዛኒያ| ቶጎ| ቻድ| ኒጄር| ናሚቢያ| ናይጄሪያ| አልጄሪያ| አንጎላ| ኢትዮጵያ| ኢኳቶሪያል ጊኔ| ኤርትራ| ኬንያ| ኬፕ ቨርድ| ካሜሩን| ኮሞሮስ| ኮት ዲቯ| ኮንጎ ሪፑብሊክ| ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ| ዚምባብዌ| ዛምቢያ| ዩጋንዳ| ደቡብ አፍሪካ| ጅቡቲ| ጊኔ| ጊኔ-ቢሳው| ጋምቢያ| ጋቦን| ጋና| ግብፅ| |