ሲ (የኮምፒዩተር ፍርገማ ቋንቋ)
From Wikipedia
ሲ የኮምፑተር ፍርገማ ቋንቋ (የተለመደ አጠራሩ ሲ) ለሲፊ አላማ የሚውል የተደራጀ ትእዛዝ ተኮር የኮምፒውትር ፍርገማ ቋንቋ ሲሆን ልዪኒክስ የሲስተም አሰሪ ተብሎ በ1970ዎቹ መጅመሪያ ላይ በደኒስ ሪቺ ተሰርቶ ቀረበ። ከዚያ ወዲህ በአብዛኛው የኮምፒዩተር የሲስተም አሰሪ ተስፋፍቶ በአለም በስፋት ከሚያገለግሉ የፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ሲ ለሎች ታዋቂ የፍርገማ ቋንቋዎች ገጽታ ላይ ታላቅ ሚና ተጫውተዋል። በተለይም ሲ++ ለሲ ማሻሻያ ተብሎ የታቀደ ቋንቋ ነው። የተመጠነና ብቃት ያለው ኮድ ለማውጣት የተመቻቸ ቋንቋ ሆኖ ሲታውቅ የሲስተም አሰሪ ሶፍትዌሮችን ለመስራት የተለመደ ቋንቋ ኦኖ ሳለ ሌሎች ሶፍትዌሮችንም ለመጻፍ በስፋት ያገለግላል።