እስልምና
From Wikipedia
እስልምና (ኢስላም) ማለት ነብዩ ሙሐመድ (የአላህ እዝነት እና ሰላም ይስፈንባቸው እና) ያስተማሩት ሃይማኖት የሚታወቅበት መጠሪያ ስም ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች ደግሞ ሙስሊም በመባል ይታወቃሉ:: ኢስላም የሚለው ጥሬ ቃል ቋንቋ 3 ትርጉሞችን ያዘለ ሆኖ እናገኘዋለን:: እነሱም
- 1ኛ ከግልጽ ወይም ስወር ከሆኑ ጉድለቶች ፍጹም ነጻ የመሆን እና የመጥራት
- 2ኛ እርቅ እና እርጋታ
- 3ኛ ሰሚነት እና ቅን ታዛዥነት የሚለውን ትርጉም አዝሎ ይገኛል
[ለማስተካከል] የኢስላም ህጋዊ ትርጉም
ኢስላም ማለት የአላህን አንድነት (ተውሂድ) ማለትም በብቸኝነት አምልኮት ሁሉ ፍጹም ለእሱ ብቻ ሊሆን የሚገባው አምላክ ማለት ነው:: በመመሪያው በማደር ለትእዛዞቹ መንበርከክ : እምነትን እና ልቦናን ለአላህ ፍጹም ማድረግ እና ከአላህ ዘንድ የመጡ መመሪያዎችን በፍጹምነት ማመን ነው::
- አንድ ሰው ሙስሊም ነው ሊባል የሚቻለው የዚህ ግዙፍ አለም ሆነ ሌላ አለ የሚባለው አለም እና በውስጧ ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ተቆጣጣሪ አስተናባሪ ብቸኛ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን እና
ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) የመጨረሻው መላክተኛ ናቸው ብሎ ማመን ነው:: ይህም በአጭር አማርኛ :- በእውነት የሚያመልኩት አምላክ ከአላህ በስተቀር የለም :: ነብዩ ሙሐመድም ባሪያው እና መላክተኛው ናቸው ብሎ ማመን ነው:: ይህም በአረብኛ «ላኢላሃ-ኢለሏህ ሙሃመድ ረሱሉሏህ» በመባል ይታወቃል:: ኢስላም እጅግ በጣም ቀላል እና ውስብስብስ ያልሆኑ መሰረታዊ የእምነት መርሆዎችን ያዘለ በመሆኑ እና ከሰው ልጅ መሰረታዊ እና ተፈጥሯዊ ፍላጎት ጋር የሚመጣተን ህግ እና ደንብ ያዘለ በመሆኑ እነሆ በዓለም ላይ ተከታዮቹ ከ1.2 ቢሊዮን በላይ ሆነው ይገኛሉ:: ኢስላም የነብያት ሁሉ ሃይማኖት መሆኑን ሙስሊሞች ጠንቅቀው ያውቃሉ።ከ አባታችን አደም ጀምሮ እነ ነብዩሏህ ኖህ ነብዩ ሙሳ እንዲሁም ሌሎች ነብያት ሙስሊሞች ነበሩ ይህ በመካ አሁን ያለው እና ካዕባ በመባል የሚታወቀው ግንብ በንብዩ አብርሃም የተሰራ በመሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እንኳ የ አብርሃም ግንብ በማለት ይጠሩታል። ይህ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር የሰው ልጆች ከ እምኔት ጎዳና እያፈነገጡ ጣኦት ማምለክ በሚጀምሩበት ወቅት ፈጣሪ በየጊዜው መልእክተኛ እየላከ ይገስጻቸው እንደነበር እና ከ ነብዩ ኢሳ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ ነብዩ ሙሐመድ መላካቸውን ኢስላም ያስተምራል።ከ ኢሳ በኋላ ነብይ እንደሚላክ በመጽሃፍፍ ቅዱስ ሳይቀር እንደተነገር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከማስረዳታቸውም በተጨማሪ ቁርአንም ቢሆን እንዴት ሰዎች ከ አረቡ አለም መልእክተኛ ይላካል ?ለምን ከ እስራኤል ወገን እንደጥንቱ አይላክምም በማለት አይሁዶች እውነታውን ካወቁ በኋላ በምቀኝንነት ኢስላምን አንቀበልም ማለታቸው እና በነብዩ ሙሀመድ መልእክት ማስተባበላቸውን በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦታል፡፤
- ኢስላም ለመረዳትም ሆነ ለማስረዳት እጅግ ቀላል ነው :: ከሌሎች እምነቶችም ልዩ የሚያደርገው የዚህን ዓለም ፈጣሪ አንድ ብቻ መሆኑን እና ሊመለክም የሚገባው ዕሱ ብቻ መሆኑን ማስተማሩ ሲሆን ለእርሱ ረዳትም ሆነ የስልጣን ተካፋይ ፈጽሞ የሌለው የሚፈልገውን ሰሪ ብቻውን ቀሪ ሃያል ጌታ አላህ ነው ብሎ ማመን ነው:: ከነብዩ ሙሃመድ ጀምሮ ሌሎች ነብያቶችም ሆኑ ታላላቅ መላእክት እንደ ጅብሪል ያሉትም እንክዋ ቢሆን የፈለጉትን የማድረግ ምንም አይነት ስልጣን የሌላቸው እና ለአላህ ፍጹም ታዛዥ መሆናቸውን ኢስላም ያስተምራል:: ስለዚህ ሙስሊሞች ነብዩ ሙሃመድንም ሆነ ሌሎችን ነብያቶች ከፈጣሪ መልእክት አድራሽ ናቸው ከማለት ውጭ በፍጹም በፍጹም አያመልኳአቸውም::
- በዚህም መሰረት ነው በኢስላም እጅግ በጣም ታላቅ ወንጀል ማለት ከአላህ ሌላ ያሉ አካላትን ማምለክ ወይም ከአላህ ጋር ሌሎችም አካላት አብረው የስልጣን ተካፋይ ናቸው ብሎ ለነሱ ማጎብደድ አላህ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው:: በይወት ዘመኑ በዚህ ወንጀል ተጸጽቶ እና ንስሃ ገብቶ እስካልተመለሰ ድረስ ከአላህ ሌላ ያለውን አካል እያመለክ የሞተ ሰው ገሃነም የዘለአለም መኖሪያው እንደሆነች እና ለሱም ምንም አይነት ረዳት እንደሌለው ኢስላም ጠንክሮ ያስተምራል:: እናም በአንድ ሃገር ሁለት መንግስት እንደማይኖር ሁሉ ይህ ዩኒቨረስም አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው ያለው በማለት ኢስላም ሌሎች እንደ ፈጣሪ ተደርገው እንዳይመለኩ ያስጠነቅቃል:: ምክንያቱም ምን ነገር ማድረግ አቅሙም ሆነ ብልሃቱ የላቸውም እና ነው::
ኢማን (የልብ ስራ) 6 መሰረታዊ ነግሮችን አተቃልሎ ይዟል::
- 1ኛ በአላህ ማመን
- 2ኛ መላእክት እንዳሉት ማመን
- 3ኛ በኪታቡ (በመጽሃፎች ማመን)
- 4ኛ በሩሱሎች ማመን
- 5ኛ በመጨረሻው ቀን_የፍርድ ቀን (ሞቶ መነሳት) እንዳለ ማመን
- 6ኛ በቀደር ማመንን
የሚሉት ሲሆኑ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው የኢስላም መሰረታዊ ነገሮች 5 ሲሆኑ
- 1ኛ አላህ አንድ ነው ሙሀመድ መላክተኛ ነው ብሎ ማመን
- 2ኛ ሰላት መስገድ
- 3ኝ ዘካ ማውጣት
- 4ና ጾም መጾም
- 5ኛ ሃጅ ማድረግ ናቸው